ከ«ኤንመርካር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
C.S. logged out
መስመር፡ 7፦
ከዚህ በላይ የኤንመርካር መንግሥት የሚገልጹ ሦስት ተጨማሪ ጽሑፎች አሉ። «''ኤንመርካርና ኤንሱሕጊርዓና''» የሚባል ተረት የኤንመርካርና የአራታ መቀያየም ሲገልጽ፣ ሐማዚ ተሸንፎ እንደ ነበር ይጠቅሳል። በ«''ሉጋልባንዳ በተራራ ዋሻ''»፣ ኤንመርካር በአራታ ላይ ዘመቻ ሲመራ ይታያል። አራተኛውና መጨረሻውም ጽላት፣ «''ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ''» ኤንመርካርና ሠራዊቱ በአራታ ዙሪያ ለ1 አመት እንደ ከበቡት ይላል። ለመሆኑ ኤንመርካር 50 አመት ከነገሰ በኋላ፣ የማርቱ ሕዝብ (አሞራውያን) በሱመርና በአካድ ሁሉ ተነሥተው ኡሩክን ለመጠብቅ ግድግዳ በበራህ መስራት እንደ ነበረበት ይጠቅሳል።
 
በነዚህ መጨረሻ 2 ጽላቶች፣ ከኤንመርካር ጦር አለቆች አንድ የሚሆን [[ሉጋልባንዳ]] የሚባል ሰው ይተረታል። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ይህ ሉጋልባንዳ «እረኛው» ኤንመርካርን ወደ ኡሩክ ዙፋን ተከተለው። ይህ ሉጋልባንዳ ደግሞ በ''[[ጊልጋመሽ ትውፊት]]'' በተባለው ግጥም ዘንድ ይህ ሉጋልባንዳ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ የ[[ጊልጋመሽ]] አባት ነበረ።
 
[[ዴቪድ ሮኅል]] የሚባል አንድ የ[[ታሪክ]] ሊቅ የኤንመርካርና የ[[ናምሩድ]] ተመሳሳይነት አመልክቷል። «-ካር» የሚለው ክፍለ-ቃል በሱመር ቋንቋ ማለት «አዳኝ» ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በ[[ኦሪት ዘፍጥረት]] ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ [[የባቢሎን ግንብ]] መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም «ባቤል» እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ።