ከ«ሻታውኳ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 5 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q119038 ስላሉ ተዛውረዋል።
No edit summary
Tags: Reverted Visual edit
መስመር፡ 3፦
'''ሻታውኳ''' በ[[አሜሪካ]] አገር በ[[1866]] ዓ.ም. የተመሰረተ የ[[ትምህርት]] እንቅስቃሴ ነው። በተለይ የታወቀው በ[[19ኛው ክፍለ ዘመን]] መጨረሻና በ[[20ኛው ክፍለ ዘመን]] መጀመርያ ሲሆን፣ አንዳንድ የሻታውኳ ተቋም እስከ ዛሬው ድረስ ስብስባ ያደርጋል። ሻታውኳ ከማስተማር በላይ ብዙ አይነት ባህላዊ መዝናናት፣ ንግግር፣ ሙዚቃ፣ ስብከት፣ ወዘተ. በማቅረቡ በተለይ ይታወቅ ነበር።
 
«ሻታውኳ» በ[[ክረምት]] ወራት ([[ጁንDecember]]፣ [[ጁላይJanuary]]ና [[ኦገስትFebruary]]) የተሰበሰበ ማኅበር ነበር። መጀመርያው ማኅበር በ[[ሻታውኳ ሐይቅ]]፣ [[ኒው ዮርክ]] ክፍላገር ነበረ። (የሐይቁ መሃል ከጫፎቹ ይልቅ ጠባብ ስለሆነ፣ የ''ሻታውኳ'' ትርጉም በኗሪዎች ቋንቋ «የታሰረ ከረጢት» ነው።) ይኸው ሻታውኳ ማኅበር «የ[[እሁድ]] ትምህርት ቤት» (የ[[ክርስትና]] ትምህርት) አስተማሪዎች መልመጃ እንዲያገኙ የታሰበ «የክረምት ሠፈር» (''ካምፕ'') ነበር። መጀመርያው የሻታውኳ ተቋም የተመሠረተው በ[[ሜቶዲስት]] ሰባኪው [[ጆን ሄይል ቪንሰንት]] እና በንግድ ሽሪኩ [[ሉዊስ ሚለር]] ነበር። ይህም ተቋም በኒው ዮርክ እስካሁን ይገኛል።
 
ለቤተሠብ ሁሉ ያገለገለ የትምህርት ክረምት ሠፈር ዕጅግ የተወደደ ሀሣብ ሆኖ፣ በአስር አመታት ውስጥ የሻታውኳ ማኅበሮች በአኅጉሩ በሙሉ ቶሎ ይስፋፋ ጀመር። በአገር ቤት በ[[ባቡር]] በሚደርሰው ሥፍራ አጠገብ ይገኙ ነበር። በቋሚ ሥፍራዎች ከተሰበሰቡት ሻታውኳዎች በላይ፣ በየመንደሩ በድንኳኖች የሚዛወሩ ሻታውኳዎች ነበሩ። ምንም ማእከላዊ ሥልጣን አልነበራቸውም፤ ስለዚህ «ነፃ ሻታውኳዎች» ተባሉ። አብዛኞቹ ሃይማኖታዊ ወይም የክርስቲያን መርሃግብር ቢኖራቸውም፣ ሌሎች ደግሞ በተለይ አለማዊ ዕውቀትና መዝናናት ያቅርቡ ነበር።