ከ«ጌዴኦ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: Reverted በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 72፦
በጌዴኦ ብሔረሰብ ሰው ሲሞት ለየት ያለ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓት ይካሄዳል። በተለይ በተለይ ወጣት ወይንም አዛውንት የሆነ ሰው ሲሞት «ዘመድ አዝማድ ሣይሰበሰብ ከተቀበረ ጥሩ አይደለም» ተብሎ ስለሚታመን እስከ ሁለት ሶስት ቀናት ድረስ አስከሬን ሣይቀበር ሊቆይ ይችላል። ሕፃናት ሲሞቱ ግን አስከሬን በዕለቱ ይቀበራል፤ ሀዘኑም የዚያኑ ዕለት እንዲያበቃ ሽማግሌዎች ቤተሰቡን ይመክራሉ፤ የሐዘን ዳርቻ እንዲያደርግላቸውም ይመርቃሉ። የዕድሜ ባለፀጋ የሆነ ሰው ሲሞት የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ከተፈፀመበት እለት ጀምሮ የሚፈፀሙ የተለያዩ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓቶች አሉ። ሁሉም የየራሳቸው የአከባበር ሥርዓት አላቸው። ከነዚህ መካከል አንዱና የመጀመሪያው በብሔረሰቡ ቋንቋ «ዊልኢሻ» ይባላል። በዚህ የሐዘን መግለጫ ሥርዓት ሟች ከተቀበረበት ዕለት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የሟች ማንነትና ያከናወናቸው ሥራዎች፣ ለሕዝቡ የፈፀመው መልካም ተግባር፣ ለጋሽነቱ፣ ሀብቱ፣ የልጆች አባትነቱ፣ ርህሩህነቱ፣ ጀግና ከሆነ ጀግንነቱ እየተገለፀ፣ በግጥም እየተገጠመ፣ እየተጨፈረ ይለቀሳል። ዊልኢሻ ከአራት እስከ ስምንት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ማታ ማታ «ጋዳ» የተባለ የሀዘን ማስረሻ ዘፈን እና ጭፈራ ሐዘንተኞች ወይንም የሟች ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ሕብረተሰብ ተሰባስበው ይጨፍራሉ። ጋዳ በሀዘን የተቆራመዱትን የሟች ዘመዶችና ቤተሰቦችን ከሀዘን ድባብ ለማውጣትና ለማጽናናት ማታ ማታ የሚከናወን ድራማዊ ጭፈራ ነው።
 
ከዚህም "በዊልኢሻ" የመጨረሻ ቀን ማታ ጀምሮ ልዩ ልዩ የተዝካር ዓይነቶች ይፈፀማሉ። የመጀመሪያው ተዝካር በብሔረሰቡ ቋንቋ /ሬንሽማ/ ሲከናወን የሚደረግ ዝግጅት ሲሆን «ሁጐ» የሚባለው ደግሞ የሟች ቤተሰብ ሙታንን የሚዘክሩበት፣ የሚያናግሩበት፣ የሟች እህት በባህል መሠረት የ«ኡማቶ» ሥርዓት በቀዳሚነት የምትፈፅምበት እንደሆነ ይነገራል። የመጀመሪያው የተዝካር ሥርዓት በተከናወነ ማግስት የቤትና የግቢ ፅዳት የሚደረግ ሲሆን ይህም «በዳኣ» ተብሎ ይጠራል። የመጨረሻው የተዝካር ዓይነት «አዋላ» በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህን ዕለት ከብት ታርዶ ከሟች የሥጋ ዘመድ በስተቀር ሌሎች የታረደውን ከብት ሥጋ በአካባቢው «ሀይቻ» አማካይነት የሚከፋፈሉበት ነው።በቀ
 
ከዊልኢሻ ቀጥሎ ያለው የለቅሶ ሥርዓት «ቡቺሣ» የሚባል ሲሆን በዚህ የለቅሶ ዓይነት ፆታን በመለየት የማስለቀስ ተግባር ይከናወናል። ሟች ሴት ከሆነች ውበቷን፣ የዋህነቷን፣ ለጋሽነቷን፣ ሙያዋን፣ እንግዳ ተቀባይነቷን ...ወዘተ እየጠቃቀሱ የለቅሶ ጭፈራ ይከናወናል። እንደዚሁም ሟች ወንድ ከሆነ ጀግንነቱን፣ ቤተሰባዊ አመጣጡን፣ ያከናወናቸውን ተግባራት /ክንውኖች/ ...ወዘተ የሚገልፁ ግጥሞችን በመደርደር ይለቀሣል፣ ይጨፈራል። ሟች ጀግና ከሆነ ለጀግንነቱ መለያ እንዲሆን «ዱፈኣ» ከተባለ ጥቁር እንጨት የሚዘጋጅ ረጅም ጊዜያዊ ሀውልት በመቃብሩ ላይ ተተክሎ በዊልአሻ ጊዜ ለጀግንነቱ መገለጫ ማቶት ተዘጋጅቶ የሰጎን ላባ ተሰክቶበት በመቃብሩ ላይ በተደረገው ጊዜያዊ ሀውልት ላይ ይንጠለጠላል። የሟችን «ሞቴ» የሚባል መቀመጫ እና «በራቴ» የሚባል የእንጨት ትራስ በመሰባበር እዚያው ሀውልት ስር በመታሰቢያነት በማስቀመጥ የሀዘን ፍፃሜ እንዲሆን ይደረጋል።
 
በጌዲኦ ብሔረሰብ ባህላዊ የለቅሶ ሥርዓት ደንብ መሠረት ለቅሶ የሚጠናቀቀው በአራተኛ ቀን ሲሆን ይህም ቀን ከሀጢያት የሚነፃበት ቀን ነው ተብሎ ይታመናል። በዚህን ዕለት የቤት ጠረጋ ሥርዓት ይከናወናል። በቤት ጠረጋው ቀን ከባልዋ ተጣልታ ወደ ወላጆቿ የመጣች ሴት ያለማንም አስታራቂ ከባሏ ጋር ተያይዛ ወደ ቤቷ ትሄዳለች። ከዚህ በተጨማሪ ዕለቱ የሟች ኑዛዜ ካለ በሕዝቡ ፊት ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቹ ተስማምተው እንዲኖሩ የሚመከሩበት የተጣላ ካለ የሚታረቅበት ዕለት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።
 
==ዋቢ ምንጭ==