ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ
ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ[1] በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓ.ም. በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነት ስላልበገረው ታላቅ ፍቅር በሰፊው ይተርካል። በተጨማሪም ደራሲው በጽሑፉ ውስጥ ሊያስተላልፉ የሞከሩት መልዕክት የሰው ልጅ በባዕድ አምልኮ ተሸብቦ ከመኖር ይልቅ ፈተናና ችግር ቢገጥሙት እንኳን ለእነዚህ ሳይበገር በአንድ አምላክ አምኖ ከጸና ድል ሊያደርግ እንደሚችል ነው።[2] ጦቢያን ወደ እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጥረቱ ተጀምሯል። ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን የትግርኛ ልብወለድ መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመው ግርማይ ነጋሽ በሚቀጥሉት ጊዚያት ጦቢያን ለመተርጎም ወደደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ አሳውቁአል።[3]
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ ብርሃነ መስቀል ደጀኔ እና ጌታሁን ሽብሩ፤ «ያሠርቱ ምእት፥ የብርዕ ምርት» ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. ገጽ 18
- ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ቅፅ 25፣ ቁጥር 5፣ 2000 ዓ.ም.፣ ገጽ 10". Archived from the original on 2011-07-20. በ2010-11-19 የተወሰደ.
- ^ Translation of the Amharic Novel, Tobiya (1907) into English.[1] Archived ኦክቶበር 22, 2018 at the Wayback Machine
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |