ሊዮናርዶ ዳቬንቺ
(ከሌኦናርዶ ዳ ቪንቺ የተዛወረ)
ሊዮናርዶ ዲ ሰር ፔሮ ዳቬንቺ (አፕሪል 15, 1452 - ሜይ 2, 1519 እ.ኤ.አ.)፣ የጣልያን ዜግነት ያለው ሰዓሊ፣ ቀራጺ፣ የፕላን ነዳፊ፣ ሙዚቀኛ፣ ተመራማሪ፣ የሂሳብ ሰው፣ ኢንጅነር፣ የመሬት ጥናት ተመራማሪ፣ የእንስሣት ጥናት ተመራማሪ እና ጸሃፊ ነበር። ሊዮናርዶ የእንደገና መወለድ የጥበብ ሰው ተደርጎ ይወሰዳል። የምድራችን የምንግዜም ምርጥ ሰአሊዎች ከሚባሉት አንዱም ነው። እንደ ሄለን ጋርድነር ገለጻ ሰአሊው ካለው ጥልቅ የማመዛዘን ችሎታና ፍላጎት ልዩ ስጦታ ከተቸራቸው የአለማችን ጥቂት ሰዎች አንዱ ነው።