ሊዝቦንፖርቱጋል ዋና ከተማ ነው።


በጥንት የከተማው ስም ኦሊሲፖ ሆኖ በአንድ ግሪክ አፈ ታሪክ መሠረት፣ ግሪኩ ጀግና ኦድሴውስ (ወይም ኡሊሴስ) ከትሮያስ (በትንሹ እስያ) ወጥቶ ባሕሮቹን ሲዞር እስከ አትላንቲክ ውቅያኖስ ድረስ ሄዶ ከተማውን ሠራ። ይሁንና ከግሪኮች በፊት የነበረ የፊንቄ ተጽእኖ በስነ ቅርስ ይታወቃል።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 2,870,208 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 545,796 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 38°44′ ሰሜን ኬክሮስ እና 09°08′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።