ሊምፋቲክ ፍላሪያሲስ
ሊምፋቲክ ፍላሪያሲስ እንዲሁም ዝሆኔ ተብሎ የሚታወቀው መነሻው በጥገኛ ትልትሎች የ ፍላሪዮአይደያ በሆነው ዝሪያ ነው. በበርካታ ክስተቶች በሽታው የህመም ምልክት የለውም። በአንዳንዶቹ ግን በእጅ፣ በእግር ወይም በመራቢያ ፍሬላይ ተለቅ ያለ እብጠት ያስከትላል. ቆዳም እየፈወረ መጥቶ ህመም ሊያስከትል ይችላል። በሽታው እንዲህ ዓይነት የሰውነት ለውጥ በሚያሰከትልበት ወቅት የተጠቃውን ሰው ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችም ይዳርጋል። [1]
Lymphatic filariasis | |
---|---|
Classification and external resources | |
A picture of a woman with elephantiasis. | |
ICD-10 | B74 |
ICD-9 | 125.0-125.9 |
eMedicine | derm/888 |
MeSH | D005368 |
መንስኤውና የምርመራ ዘዴዎች
ለማስተካከልትሎቹ (ጀርሞቹ) የሚሰራጩት በተበከሉ ትንኞችንክሻ አማካይነት ነው። በሽታው ብዙወን ጊዜ ሰዎችን የሚይይዘው በህፃንነታቸው ወቅት ነው። በሽታውን የሚያስከትሉት ትሎች (ጀርሞች) ሶስት ዓይነት ናቸው፦ ውቸረሪያ ባንክሮፍቲ፣ ብራጊያ ማላዪ፣ እና ብራጊያ ቲሞሪ። ውቸረሪያ ባንክሮፍቲ በብዛት የሚታወቅ ነው። ትሉ (ጀርሙ) የዕጢ ስርዓትንያወድማል። [1] በሽታውን በምርመራ ለማወቅ የሚቻለው በሌሊት ወቅት የተወሰደውን የደም ናሙና በ አጉሊ መነጽር ስር በማየት በማየት ነው። የደም ናሙናው በሚታይበት ወቅት The blood should be in the form of a በወፍራሙ/thick smear ሆኖ ከGiemsaጋር መቆየት አለበት። በሽታውን ለመከላከል ሰውነት የሚያመነጨውን የሰውነት መከላከያ ንጥረ ነገር ማየትም ይጠቅማል። [2]
መከላከያና ህክምና
ለማስተካከልመከላከል የሚቻለው በሽታው የሚገኝበትን ማህበረሰብ በየዓመቱ በሚካሄድ የህክምና ክትትል ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ በማድረግ ነው። ይህ ስድስት ዓመታት ያህል ይወስዳል። የሚወሰዱ መድኃኒቶች የሚያጠቃልለው አልቤንዳዞል ከ ኢንቨርሜክቲን ጋር ወይም አልቤንዳዞል ከ ዳይቲልካርባማዚንጋር ነው። መድኃኒቶቹ ያደጉ ትሎች (ጀርሞችን) አይገሉም ነገር ግን ትሎቹ በራሳቸው ጊዜ እስኪሞቱ ድረስ በሽታውን እንዳያሰራጩ ይገታሉ። በትንኝ የሚደርሰውን ንክሻ ለመከላከል የትንኞችን ቁጥር መቀነስና የአልጋ አጎበር መጠቀምን ጨምሮ ጥረት ማድረግም ይመከራል። [1]
የስርጭት አድማስ
ለማስተካከልከ120 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በዝሆኔ በሽታ ተይዘው ይገኛሉ። 1.4 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በ73 አገሮች ለበሽታ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ ይኖራሉ። በሽታው በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኝባቸው አህጉራት ደግሞ አፍሪካና ኢሲያ ናቸው። በሽታው በየዓመቱ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የኢኮኖሚ ጉዳት (እጦት) እያስከተለ ይገኛል። [1]
ዋቢዎች
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ መ "Lymphatic filariasis Fact sheet °102". World Health Organization (March 2014). በ20 March 2014 የተወሰደ.
- ^ "Parasites - Lymphatic Filariasis Diagnosis". CDC (June 14, 2013). በ21 March 2014 የተወሰደ.