ህይወት
ሕይወት ወይም ሂወት ሊባል ይችላል፣ ነገሮች ራሳቸውን ችለው እና የህይወት ክንውን አድርገው በራሳቸው እንዲኖሩ የሚያደርግ እና ህይወት ከሌላቸው እንዲለዩ የሚያደርግ ነው። ይህ ሁኔታ ሞት እስከሚከተል ድረስ ወይም ይህንን ሂደት እንዳያደርጉ እክል እስከሚገጥማቸው ድረስ ይቀጥላል። ሥነ-ህይወት የሚባለው የሳይንስ ዘርፍ ስለ ህይወት እና ህይወት ያላቸው ነገሮች የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው።
የህይወት ያላቸው ነገሮች ህልውና በዋናነት የሚረጋገጠው የነርሱ መሰረት በሆነው ህዋስ መኖር ነው። ቫይረስ ሕዋስ ስለሚያጣ ባብዛኛው እንደ ሕይወት አይቆጠርም። ይህን የሚከራክሩ ግን አሉ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |