ሄኑካ በ1ኛው ሥርወ መንግሥት በጥንታዊ ግብጽ በፈርዖኖች ሰመርኸት እና ቃዓ ዘመናት (3057-3045 ዓክልበ. ግድም) የተመዘገበ ሹም ወይም ሚኒስትር ነበር። «የንጉሥ መጥረቢያዎች አለቃ» (የንጉሥ አናጢዎች አለቃ) በሚመስል ስያሜ ይባላል። የሄኑካ ስም በነዚህ ፈርዖኖች መቃብሮች በዝሆን ጥርስ ጽላቶች እንዲህ ሲቀረጽ ተገኝቷል።
የሄኑካ መቃብር አልተገኘም።