ሀይድሮጅን
ሀይድሮጅን ኬሚካዊ ንጥረ ነገር ሲሆን ምልክቱም H አተማዊ ቁጥሩም 1 ነው። አተማዊ ክብደቱም 1.008 በመሆኑ አርኬያዊ ሰንጠረዥ ላይ ካሉት ንጥረ ነገሮች ቀላሉ ነው። ነጥበ ብርደቱ -259.16 ሴልሺየስ` ነጥበ ፍሌቱ -252.85` ነው። ስያሜውን ያገኘው በአንቶይን ላቮይሴይር ሲሆን በ1766-81 በሄንሪ ካቬንዲሽ ጥናቶቹን በማመሳከር የ ሀይድሮጅን 2 ኦክስጅን 1ን እውነትነት አረጋገጠ።