ሀይሉ ዲሣሣ
ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልሀይሉ ዲሣሣ በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. በወለጋ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ ዳሌ ዳርቦ ጃሮ ቱሉ ሰዓ በሚባለው በቄለም አውራጃ በደምቢ ዶሎ ከተማ ተወለደ።
ሀይሉ ዲሣሣ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. በሀገር ፍቅር ቲያትር በመቀጠር የኦሮምኛ ግጥምና ዜማን በመድረስ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ድራማዎች ላይ በተዋናይነት ተሳትፏል። በተቀጠረበት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትም በማገልገል ላይ ይገኛል።
የሥራዎች ዝርዝር
ለማስተካከልሀይሉ ዲሣሣ ሰባት የተለያዩ የኦሮምኛ ካሴቶችን አሳትሟል።
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 20 Archived ሴፕቴምበር 29, 2011 at the Wayback Machine