Zati qeneya
ር ምንድን ነው ? " በዛሮች ቁጥጥር ስር ምድር ወድቃለች "
ከእለታት በአንዱ ቀን የእግዚአብሔር መልእክት ወደ አዳምና ሔዋን መጣ:: ከገነት ተባረው በመሬት ላይ መመላለስ ከጀመሩ በኃላ ከመጡና የሰው ልጅ እጣፈንታ ከቀየሩ መልእክቶች አንዱ ነው:: እነኝህ ሁለት ጥንዶች 30 ጥንድ ልጆች ነበሯቸው:: እግዚአብሔር እነኝህን ልጆች ሊጎበኝ እንደሚሻ መልእክት አደረሳቸው:: የፍቃድ አምላክ ነውና:: እነርሱም ቆም ብለው ደካማ ሀሳብ አሰቡ:: " አሁን ለእግዚአብሔር ቆንጆዎቹን ልጆቻችንን ብናሳየው መርጦ ለእርሱ አገልግሎት ይወስድብናል:: ስለዚህ አስራ አምስቱን ቆንጆዎቹን ከዋሻ ውስጥ እንደብቃቸውና አስራ አምስቱን እናሳያየው " ብለው መከሩ:: አሉኝ የሚሏቸውን ልጆች ሁሉ እርሱ እንደሰጣቸው አላስተዋሉም ነበር:: እንደመከሩትም አደረጉና አስራ አምስቱን ቆንጆዎቹን መርጠው ከዋሻ ደብቀው ያልተጋነነ ውበት ያላቸውን ወደእርሱ ወሰዱ:: እግዚአብሔርም በምክራቸው አዘነ:: ከዋሻ የተደበቁት አስራአምስት ልጆችና የልጅ ልጆች እንደተሰወሩ እንዲቀሩ ረገማቸው:: ከዛች ቅፅበት አንስቶ አዳምና ሔዋን ልጆቻቸውን ማየት ተሳናቸው:: ተሰወሩ:: መንፈስ ሆኑ:: ዛር ተብለውም ተጠሩ::
ዛሮች በእኛ በምንታየው የሰው ልጆች ላይም ቅናት ያደረባቸው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ነው:: ዛሮች እንደኛው የራሳቸው ስልጣኔ አላቸው:: ይዋለዳሉ:: ስሜት አላቸው:: ያፈቅራሉ ይጠላሉ ያዝናሉ ይደሰታሉ:: በእኛና በእነርሱ መካከል ያለው ልዩነት እኛ እንታያለን እነርሱ መናፍስት ናቸው:: እኛ ስለምድር ያለን እውቀት አናሳ ነው:: ምክንያቱም ግዝፈታችን ይገድበናል:: እነርሱ ግን የማይታየን የምድር አካል ወይንም Dimension ስለሚመለከቱ ከእኛ ይልቅ የሚያውቁት አለ:: በተለይም በምድር ላይ ስላሉ ሀብቶች ጥልቅ እውቀት አላቸው:: ዛሮች