ፌሊክስ ሼልበርግ (የተወለደው እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 24 ቀን 1983) ወይም በኦንላይን ስሙ ፒውዲፓይ ስዊድናዊ ዮትዩበር ፣ ኮሜድያን እና የቪድዮ ጌም ኮሜንታተር ሲሆን በብዛት የሚታወቀው ዩትዩብ ላይ በሚለቅቃቸው ቪድዮዎች ነው።

ፒውዲፓይ
ፌሊክስ ሼልበርግ በFAX ዝግጅት ላይ እ.ኤ.አ. 2015
ፌሊክስ ሼልበርግ በFAX ዝግጅት ላይ እ.ኤ.አ. 2015
የትውልድ ቦታ ጎተንበርግ ስዊድን
የተወለዱት እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 24 ቀን 1989
ሙያ ዩትዩበር ፣ ተዋናይ
ፊርማ የ{መለጠፊያ:ስም ፊርማ


የተወለደው ጎተንበርግ ስዊድን ውስጥ ሲሆን ጎተንበርግ በሚገኘው ቻልመርስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኢንደስትሪያል ኢኮኖሚክስ እና ቴክኖሎጂ ማናጅመንት የመጀመርያ ዲግሪውን ማጥናት ጀምሮ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2010 ዩኒቨርስቲ እያለ ፒውዲፓይ በሚል ስም የዩትዩብ አካውንት ከፈተ። በቀጣዩ ዓመት በሚያጠናው የትምህርት መስክ ያለው ፍላጎት ስለቀነሰ ትምህርቱን አቋረጠ። አንድ ስካንዲኔቭያ ውስጥ የሚገኝ የማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ የሥራ ላይ ልምምድ ለማድረግ ዕድሉን ስላላገኘ ወደ ዩትዩብ ቻናሉ ላይ ለማተኮር ወሰነ። ለቪድዮዎቹም የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የፎቶሾፕ ሥራዎቹን ዕትሞች በመሸጥና በሆት ዶግ መሸጫ ውስጥ መሥራት ጀመረ። በአጭር ጊዜ ውስጥም የኦንላይን ተከታዮቹ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ። እ.ኤ.አ ጁላይ 2012 የቻናሉ ተከታዮች ቁጥር ከአንድ ሚልዮን አለፈ።

በኦገስት 15 ቀን 2013 ሼልበርግ በዩትዩብ ተከታይ ብዛት አንደኛ ሆኗል። በዛው ዓመት መጨረሻ ላይ ግን በዩትዩብ ስፖትላይት ቻናል በመበለጡ ለአጭር ጊዜ አንደኝነቱን አጥቶ ነበር። አንደኝነቱን እንደገና በእ.ኤ.አ. ዲሴምበር 23 ቀን 2013 ካገኘ ጊዜ ጀምሮ እስከ ፌብሩዋሪ 2019 ባለው መረጃ መሠረት 84 ሚሊዮን ተከታዮች አሉት። እ.ኤ.አ. ከዲሴምበር 29 ቀን 2014 እስከ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2017 ድረስ በተመልካች ቁጥር አንደኛ ነበር። እስከ እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 2019 ድረስ ባለው መረጃ መሠረት ቻናሉ 20 ቢልዮን ጊዜ የታየ ሲሆን ይህም በዩትዩብ ላይ ብዙ ተመልካች ካላቸው ቻናሎች ውስጥ 8ኛ አድርጎታል።