ጀርመናዊ ቋንቋዎች
ጀርመናዊ ቋንቋዎች የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ሲሆን፣ ሁላቸው ከቅድመ-ጀርማንኛ ደረሱ።
የጀርመናዊ ቋንቋዎች ፫ ክፍሎች ምዕራብ ጀርመናዊ፣ ስሜን ጀርመናዊ፣ እና ምሥራቅ ጀርመናዊ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ ምሥራቅ ጀርመናዊ አሁን ጠፍቶ አይገኝም።
ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎችEdit
ዋና ቋንቋዎቹ እንግሊዝኛ፣ ሆላንድኛ፣ እና ጀርመንኛ ሲሆኑ፣ በነዚህ ውስጥ አያሌ ንዑስ ቀበሌኞች አሉ። ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች ይዩ።
ስሜን ጀርመናዊ ቋንቋዎችEdit
እነዚህ ሁላቸው ከጥንታዊ ኖርስኛ ደረሱ። አሁን ዋናዎቹ ኖርዌይኛ፣ ስዊድኛ፣ ዳንኛ፣ አይስላንድኛ፣ ፋሮኛ ናቸው።
ምሥራቅ ጀርመናዊ ቋንቋዎችEdit
እነዚህ ቋንቋዎች አሁን አይገኙም። ጎትኛ፣ የክሪሜያ ጎትኛ፣ ቫንዳልኛ፣ እና ቡርጉንድኛ ምሥራቅ ጀርመናዊ ልሳናት ነበሩ።