ይምርሃነ ክርስቶስ
ይምርሃነ ክርስቶስ በ ዓፄ ይምርሃነ ክርስቶስ አነሳሽነት በ12ኛው ክፍለ ዘመን በአቡነ ዮሴፍ ተራራ ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ የተሰራ ቤተክርስቲያንና በዚያው ዋሻ ውስጥ ከቤተርክስቲያኑ ፊትለፊት ያለ ቤተ መንግስት ህንጻ በአንድነት የሚጠሩበት ስም ነው። ዋሻው ከላሊበላ የ6 ሰዓት የእግር ጉዞ ርቀት ላይ ይሚገኝ ሲሆን 45ሜትር ርዝመት በ6 ሜትር ቁመትና 50ሜትር ጉድጉደት አለው። በዋሻው ውስጥና ውጭ ለጸበል የሚያገለግሉ ምንጮች ይፈልቁበታል። ዓፄ ይምርሃነ ክርስቶስ ከሮሃ ሆኖ አገሩን ያስተዳድር እንጂ ይሄው ቤተክርስቲያንና ቤተመንግስት ሲታነጽ መኖሪያውን ወድዚህ ዋሻ እንዳዛወረ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ የህይወት ታሪኩ ይገልጻል። በ16ኛው ክፍልዘመን መጀመሪያ ኢትዮጵያን ጎብኝቷት የነበረው አልቫሬዝ እንዲሁ በዚህ ቤተክርስቲያን ለ2 ቀን ቆይታ በማድረግ ገድለ ይምርሃነ ክርስቶስ የተሰኘ መጽሐፍ እንዳነበበና እንደመረመረ ያትታል[1]።
| ||||
---|---|---|---|---|
ይምርሃነ ክርስቶስ | ||||
[[ስዕል:|250px]] | ||||
ከግራ ወደቀኝ፡ መቃብሮች፣ ቤተክርስቲያን፣ ቤተመንግስትና አጽማት ማረፊያ | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | ዋሻ ውስጥ የሚገኝ | |||
አካባቢ** | አቡነ ዮሴፍ ተራራ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን | 12ኛው ክፍለ ዘመን | |||
አደጋ | ቤተመንግስት ጣራና ወለል | |||
* የአለበት ቦታ ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
ለማስተካከልከፍ ብሎ የተጠቀሰው ድርሰት፣ የይምርሃነ ክርስቶስ ሁለት ህንጻዎች ከመሰራታቸው በፊት ዋሻው ዛፎች የበቀሉበትና ከስሩም ትንሽ ሐቅይ እንደነበረበት ያትታል። በዚህ ሐይቅ ላይ እንጨት ርብራብ በማድረግና ከዚያም ላይ አፈር በመነስነስ የበተክርስቲያኑ መሰረት እንደተጣለ ይነገራል። ከመሰረቱ በኋላ የማገርና የድንጋይ ልውውጥ በሚታይበት መልኩ ወደላይ የተገነባ ሲሆን ይህ አሰራሩ ደብረ ዳሞን ያስታውሳል። ድንጋዩ ነጭ ፕላስተር የተቀባ ስሆን መስኮቶቹ ግን ከነጭ ደንጊያ ወይንም ከእንጨት የተስሩ ናቸው።
የቤተክርስቲያኑ ህንጻ 3 መግቢያዎች ሲኖሩት በሰሜን(ለወንዶች)፣ ደቡብ(ለሴቶች) እና ምሥራቅ (ለካህናት) ይገኛሉ። በግድግዳው ላይ የሚገኙ፣ ነገር ግን በአቧራ የተሸፉኑት ምስሎች ከዚሁ ዘመን የሚመነጩ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የግድግዳ ምስላት ቀደምት ናቸው።
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ይህን ቤተክርቲያን በ16ኛው ክፍለዘመን መግቢያ ላይ የጎበኘው ሲሆን፣ እንደርሱ ዘገባ በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኑ 200 ደብተራዎች የነበሩት ሲሆን አጠቃላይ ቤቱ በሊቀ ካህናት ይመራ እንደነበር ሲጠቅስ፤ በወቅቱ መነኮሳት እንደማይኖሩበትም ዘግቧል[3]።
ይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ መንግስት
ለማስተካከልየይምረሃነ ክርስቶስ ቤ/መንግስት ከቤ/ክርስቲያኑ ያነሰ ጥራት ያለውና በአሁኑ ወቅት ለመፍረስ አደጋ የተጋለጠ ነው። ሁለት የጣራው ክፍሎች የተደረመሱ ሲሆን የአንዱ ፎቅ ወለልም እንዲሁ ተደርምሷል።
ከይምርሃነ ክርስቶ ቤ/ክርስቲያን ጀርባ 3 መቃብሮች ሲኖሩ፣ የራሳቸው የዓፄ ይምርሃነ፣ የሴት ልጃቸው እና ከእስክንድርያ ንጉሱን ሊጠይቁ የመጡ ፓትሪያርክ እንደሆኑ ይጠቀሳል። ወደዋሻው ውስጥ በጣም ርቆ ደግሞ የብዙ ምዕመናን አጽም የሚታይበት ሰፊና ጨለማ ክፍል አለ።
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ Stuart Munro-Hay, Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide, I.B.Tauris & Co, London, 2003(page 225)
- ^ Yemrehannä Krestos church − documenting cultural heritage in Ethiopia, CHW Heritage without Borders Cultural BKULTURARV UTAN GRÄNSER, 2010
- ^ Stuart Munro-Hay, Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide, I.B.Tauris & Co, London, 2003(page 225)
ዋቢ ጽሑፍ
ለማስተካከል- Yemrehannä Krestos church − documenting cultural heritage in Ethiopia, CHW Heritage without Borders Cultural BKULTURARV UTAN GRÄNSER, 2010 (በኢንተርኔት )