የአለቃ የልጅ ልጅ

(71)ነገሩ የሆነው ፎገራ ውስጥ ሲሆን በደርግ ዘመን ነው። ካድሬው ህዝቡን ሰብስቦ ስለ መንደር ምስረታ አስፈላጊነት ሲያብራራ «በመንደር ከሰፈራችሁ ውሃና መብራት በየቤታችሁ ይገባላችኋል» እያለ ከቀሰቀሰ በኋላ የህዝቡም ተቃውሞ አዳማጭ ሳያገኝ ሰፈሩ ሜዳ ላይ ተሰርቶ ሕዝብ ሰፈረ። ክረምት ሲመጣም ጣና ሐይቅ እንደተለመደው የፎገራን ሜዳ ቤቴ ብሎ ሲያጥለቀልቀው ህዝቡ ወደ በአካባቢው ከተሞች ተሰደደ። በዛን ወቅት የአለቃን የልጅ ልጅ ጋዜጠኛ አግኝቶ ስለ ሁኔታው ሲያነጋግረው «ያው በካድሬው እንደተነገረን ውሃው በየቤታችን ገብቷል መብራቱ ብቻ ነው የቀረው» ብሎ አስተያየቱን ሰጠ።