የሙፍቲ ዳውድ የህይወት ታሪክ

አል-ጀበርት የአርጎብኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት/ Al Jebert Argobban languege School ሙፍቲ ዳውድ ሀበሾችን’ና ኢማም አል-ሻፊዒይን ያስተሳሰረ

  1. የአርጎባ_ዓሊም

▂▂▂▂▂{ውዱ ታሪካችንን ያንብቡት}▂▂▂▂▂ ታሪካችን በታላላቅ ኢስላማዊ ስብእናዎች ያሸበረቀ፤ በጠካራዎቹ ሙእሚኖች አስደናቂ ገድል የተሞላ ነዉ፡፡ ከነዚህ ልብን ከሚነኩ’ና ስለ ማንነታችን ቆም ብለን እንድናስብ ከሚጋብዙን ነገር ግን በእጅጉ ከተረሱ ታኮቻችን ዉስጥ አንዱን አነሆ!! ከ300 ኪታብ በላይ በእጃቸዉ የፃፉ የአርጎባ ዓሊም፤ለዚህም ገና የመን ዘቢድ ትምህርት ላይ እያሉ የሐበሻ ሙፍቲ ሸምሰል ሀበሻ ባሕሩ ራሕመቲ ኢማሙ አዕዞም ፊል ሀቂቀት ተብሎ የተመሰከረላቸዉን ታዋቂዉ ዓሊምና ምሁር የሐጂ ሙፍቲ ዳዉድን የሂይወት ታሪክ እንዲህ ልንተርከዉ ነዉ አብራችሁኝ ሁኑ፡፡ወቢላሂ ተዉፊቅ!!!

  1. ክፍል_አንድ

ስማቸዉ ሙፍቲ # ዳዉድ_ቢን_አቡበክር አል-ጀበርቲ ይባላል፡፡ሙፍቲ ዳዉድ የተወለዱት በአሁኑ አከላለል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ከዞኗ ርዕሰ መዲና ከሚሴ ከተማ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ልዩ ቦታዋ ገዶ በምትባል መንደር ሲሆን የተወለዱትም እንደ ሒጅራ አቆጣጠር በ1134 ወይም እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር በ1735 ዓመተ ልደት ነበር፡፡ ገዶ ከሙፍቲ ዳዉድ በተጨማሪ እንደ ሐጂ ከቢር አሕመድ አልሙቅሪዕ የመሳሰሉትን ታላላቅ ዑለሞችንም አፍርታለች፡፡ ሙፍቲ ዳዉድ በየመናዊያን ተማሪዎቻቸዉ'ና ደረሶቻቸዉ ዘንድ ሶስት የተለያዩ መጠሪያ ስም የነበራቸዉ ሲሆን እነሱም፡- ሙፍቲ ዳዉድ ሙፍተል ሀበሽ(የሀበሻዉ ሙፍቲ) ሙፍተል ዓናም (ፈትዋው ሰዎችን የሚጠቅም ሙፍቲ) በመባል ይታወቃሉ፡፡ በትዉልድ ሀገራቸዉ ላይ የተለያዩ መሰረታዊ የሚባሉትን ኢስላማዊ እዉቀቶች በመማር የልጅነት ጊዚያቸዉን አሳለፉ፡፡ ሆኖም ግን በዘመኑ የነበረዉ የትምህርት አሰጣጥ የሙፍቲን ጣሪያ የነካ የዒልም ፍላጎት የሚያረካ አልነበረም ፡፡ስለሆነም ሙፍቲ የእዉቀት ጥማቸዉን ሊያስታግስላቸዉ ወደሚችል የትምህርት ተቋም ለመሄድ ወሰኑ፡፡እሱም የመን ሀገር የሚገኘዉና በጊዜዉ አለማችን ላይ አለ የሚባል እዉቅና ገናና የነበረዉ ዘቢድ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ነበር፡፡ በዘቢድ ሸለቆ ስም የተሰየመችዉ ዘቢድ ከተማ በባህላዊ የቤቶች አአሰራር ፤ በጠባብ መንገዶቿና በጡብ ባጌጡ ህንፃዎቿም ትታወቃለች ፡፡ከ13ኛዉ እስከ 15ኛዉ ክፍለ ዘመን ድረስ የየመን ዋና ከተማ በመሆንም አገልግላለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዘቢድ ከተማ እጅግ በጣም ብዙ ከፍተኛ የሆነ የመስጂድ ማእከላት የነበሯት ሲሆን ቁጥራቸዉም 86 ይደርስ ነበር፡፡በከተማዋ ምእራባዊ አቅጣጫ የተገነባዉ’ና የመጀመሪያዉ መስጂድ ተብሎ የተመዘገበዉ አል-ኣሻ’ዒር መስጂድ ደግሞ ግዙፉና ለከተማዋም ድምቀትን ፈጥሮላት የኖረ መስጂድ ነዉ፡፡ አል-አሻ’ዒር መስጂድ የተገነባዉ የነቢዩ ሙሀመድ ﷺ ሱሀባ በነበሩት አቡ ሙሳ አሻ’ዓሪ(ረ ዐ) ሲሆን የተገነባዉም እ.እ.አ በ628 AD ነበር፡፡አል-አሻ’ዒር መስጂድ በኢስላም ታሪክ ዉስጥ ከተገነቡት መስጂዶች ዉስጥ አምስተኛዉ መስጂድ ተደርጎ ተመዝግቧል:: ከተማዋ ግዙፉንና ዝነኛዉን የዘቢድ ዩኒቨርሲቲን አቅፋ በመያዟና የተለያዩ ኢሰላማዊ ትምህርቶችም በስፋት ይጎርፍባት ስለነበር ከተማዋን ዐረቦች’ና የአለም ሙስሊሞች ዋና ማእከላቸዉ(መናገሻቸዉ) አድርገዋት ነበር። ስለ ዘቢድ Encyclopaedia Britannica እንዲህ ሲል አስፍሮታል፡፡’’Zabid was the capital of Yemen from the 13th to 15th century and a centre of the Arab and Muslim world due in the large part to its famed University of Zabid and being a centre of Islamic education.’’ እናም ሙፍቲ ዳዉድ ይህንን ታላቅ ማእከል ገና በለጋ እድሚያቸዉ ተቀላቀሉት፡፡ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥም ለአስራ ስድስት አመታት ያክል ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ከቆዩ ቡኃላ እዚያዉ ዘቢድ ዉስጥ ለሁለት አመትና ከዛ በላይ በሌክቸርነት (በአስተማሪነት) ሙያ አግልግለዋል፡፡ ሙፍቲ ዳዉድ የሙፍቲነት ማእረግን የተጎናፀፉት እዚያዉ ዘቢድ ዉስጥ ሲሆን በሀበሻ ምድር ላይ

  1. የመጀመሪያዉ_ሙፍቲ ለመሆንም በቅተዋል፡፡

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያ ፈትዋ ሰጪ በመሆን ከሸይኾቻቸዉ ኢጃዛ(ፍቃድ) የተሰጣቸዉና በይ’ዓህ የገቡ ናቸዉ፡፡(ራህመቱላሒ ዓለይህ!!!) ሙፍቲ ዳዉድ የሙፍቲነትን ማእረግ ያገኙባቸዉን ታላላቅ ታሪኮችና የእዉቀት ማእዶች አሏቸዉ፡፡ከታሪኮቻቸዉ ዉስጥ አንዱን ላጫዉታቹህ፡- የመን ዉስጥ አንድ አሳዳሪ(ጌታ) እና ሰራተኛዋ……… ... ግን ለምን ነገ አንቀጥለዉም?? ቀጣዩ ክፍል እጅግ መሳጭ ሰለሆነ በናፍቆት ይጠብቁን! ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ || ይቀጥላል...||