ዞራስተር በጥንቱ የፋርስ ግዛት (ያሁኑ ኢራን) የኖረ የዛራጡሽትራ ሃይማኖት መስራች ነበር። ሃይማኖቱ በጣም ረጅም ታሪክ የነበረውና በሳሳሲን ስርወ መንግስት የፋርስ አገር ብሄራዊ ሃይማኖት ነበር። አብዛኛው ተመራማሪወች እንደሚስማሙ፣ ዞራስተር በርግጥ በህይወት የነበረ ሰው ነው። በግምት ከዛሬ 3200 አመት በፊት እንደኖረ (ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ13ኛው ክፍለ ዘመን) ይተመናል። ሆኖም ግን ይህ እርግጠኛ ጊዜ አይደለም፣ አንዳንዶች የነቢዩን ዘመን ከ18ኛው እስከ 9ኛው ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበሩ ክፍለ ዘመኖች በአንዱ ሊኖር እንዲችል ይገምታሉ።

የሰው ልጅ አጠቃላይ ሁኔታ በአዕምሮው ውስጥ በሚካሄድ የ"አሻ" (እውነት)ና የ"ድሩይ" (ውሸት) ግጭቶች የሚወሰን ነው። ፈጠራ፣ ኅልውነት፣ ነጻ ፈቃድ፣ የተፈጥሮ (ሥነ ፍጥረታዊ) ሕግ -- እኒህ ሁሉ አሻ (እውነት) ይባላሉ። ባጠቃላይ መልኩ የክፉና ደግ አስተሳሰቦችን ያፈለቀ ነቢይ ነው። ሁሉም ነገር የክፉ ወይም የደግ ዋጋ ሳይሰጠው በፊት ሁሉም ነገር የተፈቀደ ነበር። የዞራስተር ፈጠራ ለራሱ ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በአይሁድ ሃይማኖትም ላይ ተጽዕኖ በማሳረፍ በክርስትናና አሁን በምንኖርበት አለም አስተያየቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርጋል። ብዙ ፈላስፋወች፣ እንደ ስፒኖዛሄራክሊተስፕላቶ ከዚህ ሰው ትምህርት ቀስመዋል።

ጥቅስ፦

  • «ፈቃድና ኃይል ሲኖረኝ፣ የአሻ ፍላጎት አስተምራለሁ።» -- ጋጣ (ያስና 28:5)