ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 18
መጋቢት ፲፰
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - ዓፄ ዮሐንስ እና የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ወሎ፣ ቦሩ ሜዳ ላይ ተገናኝተው ንጉሥ ምኒልክ የንጉሠ ነገሥቱን የበላይነት መቀበላቸውን እና ዓፄ ዮሐንስ ደግሞ የምኒልክን በሸዋ ላይ ንጉሥነታቸውን በመቀበል በመሐላ ታረቁ። ንጉሠ ነገሥቱ ለንጉሥ ምኒልክም ዘውድ ጫኑላቸው።
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - በፋሺስት ኢጣሊያና በአርበኞች መካከል በፉግታ ውጊያ ተካሄደ።
- ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - የሆላንድ 'ኬ.ኤል.ኤም' 'ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ እና የ'ፓን-አም' ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ በ'ካናሪ ደሴቶች፤ ቴኔሪፍ ጥያራ ጣቢያ ማኮብኮቢያ ላይ በጉም ምክንያት ተጋጭተው፣ የ'ኬ.ኤል.ኤሙ' ፪መቶ፵፰ ተሣፋሪዎች በሙሉ ሲሞቱ ከ'ፓን-አሙ' ተሣፋሪዎች መኻል ፫መቶ፴፭ ሞተው ፷፩ ሰዎች ተርፈዋል። ይኼ አደጋ በታሪክ ከተከሰቱት የጥያራ አደጋዎች በሙሉ እጅግ የባሰ አደጋ በመሆን ይታወቃል።