ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶፮ - ፶፰ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፬ ሲሆን በ፳፬ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። የሚያተኩረውም የአብርሃም እምነት ላይ ነው ።

ወደ ሮማውያን ፬
በ፶፮ ፶፰ ዓ.ም. ወደ ሮማውያን በፖፒረስ ፵ ወረቀት ላይ የተጻፈ መልዕክት ። ይህም የሚያሳየው ስብርባሪውን ነው
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የአብርሃም እምነት ለማስተካከል

ቁጥር ፲፪ - ፳፫ በግርም ሁኔታ ያብራራዋል ።


ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፬

ቁጥር ፩ - ፲ ለማስተካከል

1፤እንግዲህ፡በሥጋ፡አባታችን፡የኾነ፡አብርሃም፡ምን፡አገኘ፡እንላለን፧ 2፤አብርሃም፡በሥራ፡ጸድቆ፡ቢኾን፡የሚመካበት፡አለውና፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አይደለም። 3፤መጽሐፍስ፡ምን፡አለ፧አብርሃምም፡እግዚአብሔርን፡አመነ፡ጽድቅም፡ኾኖ፡ተቈጠረለት። 4፤ለሚሠራ፡ደመ፡ወዝ፡እንደ፡ዕዳ፡ነው፡እንጂ፡እንደ፡ጸጋ፡አይቈጠርለትም፤ 5፤ነገር፡ግን፥ለማይሠራ፥ኀጢአተኛውንም፡በሚያጸድቅ፡ለሚያምን፡ሰው፡እምነቱ፡ጽድቅ፡ኾኖ፡ ይቈጠርለታል። 6፤እንደዚህ፡ዳዊት፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ያለሥራ፡ጽድቅን፡ስለሚቈጥርለት፡ስለ፡ሰው፡ብፅዕና፡ይናገራል፡ እንዲህ፡ሲል፦ 7፤ዐመፃቸው፡የተሰረየላቸው፡ኀጢአታቸውም፡የተከደነላቸው፡ብፁዓን፡ናቸው፤ 8፤ጌታ፡ኀጢአቱን፡የማይቈጥርበት፡ሰው፡ብፁዕ፡ነው። 9፤እንግዲህ፡ይህ፡ብፅዕና፡ስለ፡መገረዝ፡ተነገረ፧ወይስ፡ደግሞ፡ስላለመገረዝ፧እምነቱ፡ለአብርሃም፡ጽድቅ፡ ኾኖ፡ተቈጠረለት፡እንላለንና። 10፤እንዴት፡ተቈጠረለት፧ተገርዞ፡ሳለ፡ነውን፧ወይስ፡ሳይገረዝ፧ተገርዞስ፡አይደለም፥ሳይገረዝ፡ነበር፡ እንጂ።

ቁጥር ፲፩ - ፳፬ ለማስተካከል

11፤ሳይገረዝም፡በነበረው፡እምነት፡ያገኘው፡የጽድቅ፡ማኅተም፡የኾነ፡የመገረዝን፡ምልክት፡ተቀበለ፤ይህም፡ እነርሱ፡ደግሞ፡ጻድቃን፡ኾነው፡ይቈጠሩ፡ዘንድ፡ሳይገረዙ፡ለሚያምኑ፡ዅሉ፡አባት፡እንዲኾን፡ነው፥ 12፤ለተገረዙትም፡አባት፡እንዲኾን፡ነው፤ይኸውም፡ለተገረዙት፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥አባታችን፡ አብርሃም፡ሳይገረዝ፡የነበረውን፡የእምነቱን፡ፍለጋ፡ደግሞ፡ለሚከተሉ፡ነው። 13፤የዓለምም፡ወራሽ፡እንዲኾን፡ለአብርሃምና፡ለዘሩ፡የተሰጠው፡የተስፋ፡ቃል፡በእምነት፡ጽድቅ፡ነው፡እንጂ፡ በሕግ፡አይደለም። 14፤ከሕግ፡የኾኑትስ፡ወራሾች፡ከኾኑ፡እምነት፡ከንቱ፡ኾኗል፡የተስፋውም፡ቃል፡ተሽሯል፤ 15፤ሕጉ፡መቅሠፍትን፡ያደርጋልና፤ነገር፡ግን፥ሕግ፡በሌለበት፡መተላለፍ፡የለም። 16-17፤ስለዚህ፥ከሕግ፡ብቻ፡ሳይኾን፥ከአብርሃም፡እምነት፡ደግሞ፡ለኾነ፣ለዘሩ፡ዅሉ፥የተስፋው፡ቃል፡ እንዲጸና፡እንደ፡ጸጋ፡ይኾን፡ዘንድ፥በእምነት፡ነው፤ርሱም፦ለብዙ፡አሕዛብ፡አባት፡አደረግኹኽ፡ተብሎ፡ እንደ፡ተጻፈ፥ለሙታን፡ሕይወት፡በሚሰጥ፡የሌለውንም፡እንዳለ፡አድርጎ፡በሚጠራ፡ባመነበት፡በአምላክ፡ፊት፡ የዅላችን፡አባት፡ነው። 18፤ዘርኽ፡እንዲሁ፡ሊኾን፡ነው፡እንደ፡ተባለ፥ተስፋ፡ባልኾነው፡ጊዜ፡የብዙ፡አሕዛብ፡አባት፡እንዲኾን፡ ተስፋ፡ይዞ፡አመነ። 19፤የመቶ፡ዓመትም፡ሽማግሌ፡ስለ፡ኾነ፡እንደ፡ምውት፡የኾነውን፡የራሱን፡ሥጋና፡የሳራ፡ማሕፀን፡ምውት፡ መኾኑን፡በእምነቱ፡ሳይደክም፡ተመለከተ፤ 20-21፤ለእግዚአብሔርም፡ክብር፡እየሰጠ፥የሰጠውንም፡ተስፋ፡ደግሞ፡ሊፈጽም፡እንዲችል፡አጥብቆ፡ እየተረዳ፥በእምነት፡በረታ፡እንጂ፡ባለማመን፡ምክንያት፡በእግዚአብሔር፡ተስፋ፡ቃል፡አልተጠራጠረም። 22፤ስለዚህ፡ደግሞ፥ጽድቅ፡ኾኖ፡ተቈጠረለት። 23፤ነገር፡ግን፦ተቈጠረለት፡የሚለው፡ቃል፡ስለ፡ርሱ፡ብቻ፡የተጻፈ፡አይደለም፥ስለ፡እኛም፡ነው፡እንጂ፤ 24-25፤ስለ፡በደላችን፡ዐልፎ፡የተሰጠውን፥እኛን፡ስለ፡ማጽደቅም፡የተነሣውን፥ጌታችንን፣ኢየሱስን፡ ከሙታን፡ባስነሣው፡ለምናምን፡ለእኛ፡ይቈጠርልን፡ዘንድ፡አለው።