ወልወል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ፥ በሶማሌ ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች ። ከተማዋ ከባህር ወለል በአምስት መቶ ሰባ ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን 7°03′ ሰሜን ኬክሮስ እና 45°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ትገኛለች።

ወልወል
ከፍታ 570 ሜትር
ወልወል is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ወልወል

7°03′ ሰሜን ኬክሮስ እና 45°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በኦጋዴን ክልል በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያዊ ሶማልያ ያለውን ድንበር እንዲያሠምሩ የተላኩት የብሪታንያ እና የኢትዮጵያ ልዑካን በዚሁ ክልል ውስጥ ለሥራ ይዘጋጁ ነበር። በዚህ ጊዜ ‘ሙስቲ’ በሚባል የኢጣሊያ መቶ ዓለቃ የሚታዘዙ ሁለት መቶ ሶማሌያዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፤ ከሺህ በላይ የውሐ ጉድጓዶች የነበሯትን፤ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ያለችውን ወልወልን ከበዋት ተገኙ። በወቅቱ የኦጋዴን ገዥ የነበሩት የፊታውራሪ ሺፈራው ወታደሮችና የኢጣልያን ወገን በሚመራው በሻለቃ ቺማሩታ ወታደሮች ለሁለት ሣምንታት ከተፋጠጡ በኋላ በኢትዮጵያና በፋሽስታዊ ኢጣልያ መካከል ለአምሥት ዓመታት የተከተለው ጦርነት ክብሪት ተጫረ።

የፋሺስት ኢጣሊያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ለብዙ ዓመታት አገራችንን በኃይል ወርሮ ቅኝ ግዛት ለማድረግ ሲያቅድ የነበረውን ዓላማ በዚህ ግፍ ካካሄደ በኋላ በዓመቱ በጥቅምት ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በዚያው በኦጋዴን መሥመር ወረረ።