ኤፌሶን
ኤፌሶን (ግሪክኛ፦ Ἔφεσος /ኤፈሶስ/) በጥንታዊ ኢዮኒያ የነበረ ከተማ ሲሆን አሁን በቱርክ አገር ያለው ሰፊ ፍርስራሽ ቦታ ነው።
ኤፌሶን Ἔφεσος | |
---|---|
![]() | |
ከሮማውያን ዘመን (120 ዓ.ም.) የተሠራው የኤፌሶን መጻሕፍት በት ፍርስራሽ | |
ሥፍራ | |
ዘመናዊ አገር | ቱርክ |
ጥንታዊ አገር | ኢዮኒያ |
በኬጥያውያን መንግሥት ዘመን፣ ከተማው አፓሳ ተብሎ የኬጥያውያን ጎረቤት በስተምዕራብ የአርዛዋ (የቀድሞ «ሉዊያ») ዋና ከተማ ነበረ። ኬጥያውያን አርዛዋን በኋላ ቢጨምሩም፣ ኤፌሶን የግሪኮች (ኬጥኛ፦ «አሐያ») ግዛት ውስጥ ሆነ።