ኤታና

የጥንት ሜሶጶጣሚያ ንጉሥ

ኤታናሱመር ነገሥታት ዝርዝር ላይ 12ኛው የኪሽ ንጉሥ በሱመር፣ የማሽዳ ልጅ አርዊዩም ተከታይ ይባላል። ከዚህ በላይ «ወደ ሰማይ ዐርጐ ውጭ አገሮችን ሁሉ ያሠለጠነው» ይባላል። 1,560 አመታት (ወይም እንደ ሌላ ቅጂ 635 አመታት) ከነገሠ በኋላ በልጁ ባሊኅ ተከተለ። ለኤታና ኅልውና የሥነ ቅርስ ማረጋገጫ ገና ባይገኝም፣ ስሙ ከአንዳንድ ሌላ የትውፊት ጽላት ይታወቃል። አንዳንዴም ይህ ኤታና የኪሽ መጀመርያው ንጉሥና መስራች ይባል ነበር።