አሉባልታ

ሶስት ጓደኛሞች ወደ እሩቅ ሀገር ለመሄድ ተነሱ። ለመንገድ የሚያስፈልጋቸውን ስነቅ ፣ ወሀና ሌላም ነገሮች ያዘው ጉዞ ጀመሩ።ስማቸው ከዚህ እንደሚከተለው ነው።

ሙማዚስ፣አሩአሣ እና ጀጎን ይባላሉ።ሙማዚስና ጀጎን አብሮ አደግ ጓደኛሞች ናቸው።

ጀጎንም ለምሳ ተቀምጠው እየተመገቡ እያለ "በመንገድ የሚገጥመንን ማንኛውንም ችግር በጋራ ነው የምን ጋፈጠው" ሲል ሙማዚስ ደስ ብሎት ተቀበለ።

አሩአሣ ግን ማንን አምኖ በአፉ "ይሁን"ቢልም በልቡ ግን ሞኛችሁን ፈልጉ አለ። ስንሻቸውን እየተጋገዙ ይይዙታል ውሃቸውንም እንደዛው ።

ከመሀከላቸው ሙማዚስ ሽንት ሊወጣ ወደ ጫካው በገባ ጊዜ አሩአሣ ለጀጎን "ጀጎን ሙማዚስ ያለኝን ብትሰማ ለካስ እንደዚህ ክፉ ነው ! እንዴት ባንተ በጓደኛው ላይ እንደዚህ ያስባል።" ብሎ ሁለቱን ጓደኛሞች ማቀሳሰር ጀመረ። "ምንም አላለም ዝም በል ጓደኛዬን አውቀዋለው" ብሎ ሲመልስለት ደንገጥ ብሎ "ምን አለ መሰለህ ‛የሆነ አውሬ ካገኘን ቀድመን ጀጎንን እን ጥለውና እኛ እና መልጣለን ’ አይለኝም መሰለህ እኔማ ተው አብረን እናምልጥ ስለው ‛እሱን ስለማታውቀው ነው እንደዚህ አይነት ነገር ከመጣ አሳልፎ ይሰጠናል’ አለኝ አንተ እንደ ዚህ አይነት ሰው ነህ እንዴ?" አለ

አሩአሣ ሙማዚስ እንደዚህ ብሎት ሳይሆን መንገድ ላይ ለሚገጥማቸው ችግር አንዱን አሳልፎ ሰጥቶ እራሱን ነፃ ለማድረግ ካለው ጉጉት የተነሳ ነው ።

ጀጎን ዝም ብሎ ሲሰማው ከቆየ በኋላ በጥሞና ጥቂት አሰበና መለስ ብሎ "ስማ ወንድሜ በእኔና በእሱ መሀከል ንፋስ እንዲገባ አልፈቅድም ። በምንም ተአምር ሙማዚስ በኔ ላይ ክፉ ሀሳብ የለውም። ከዚህ በኋላ ስለሱ ይህን አለህ ብትለኝ እንጋጫለን። ተግባባን " ሲለው ተስፋ ቆርጦ ተወው

ጓደኛቸውን ጠብቀው መንገዳቸውን ቀጠሉ ብዙ ርቀት ከተጓዙ በኋላ ምግብ ለመመገብ አንድ ዛፍ ስር ተቀመጡ። ምንም ያህል ሁለቱ በተነጋገሩት ነገር ቢቀያየሙም ሙማዚስ ምንም ነገሩን ስለማያውቅ አንድ ላይ ተመገቡ። ከጨረሱ በኋላ ጉዞ ሲጀምሩ ጀጎን ሽንቱን ሊሸና ካጠገባቸው ብዙም ሳይርቅ ገሸሽ ብሎ መሽናት ሲጀምር።

አሩአሣ ቀለስለስ ብሎ " ሙማዚስ ጀጎን በነፍስህ ሊጫወትብህ ነው። ምን እንዳለኝ ብነግርህ....."

"ሰውዬው ነገር እንዳታመጣ ምን አለኝ ልትል ነው?" አለ ሙማዚስ

ለጀጎን የነገረውን በሙሉ ገልብጦ ለሙማዙስም ሲ ነግረው ሙማዚስ"ስማ ጀጎንን አውቀዋለው አንተ ትላንት ነው የተቀላቀልከን ከሱ ጋር አፈር ፈጭተን ጭቃ አብኩተን አብረን ነው ያደግ ነው። " በዚህ ጊዜ አሩአሣ ተስፋ ቢቆርም ካፈርኩ አይመልሰኝ ቀሚመስል ነገር "ሲመጣ እንጠይቀው አለ? " አለ አሩአሣ

"ይቻላል ።" ብሎ በጓደኛው ላይ ያለውን አመኔታ ገለፀለት

ከሽንት እንደመጣ እሳት መስለው ተኮራርፈው ጠበቁት ሙማዚስም ፊቱን ቋጠር አድርጎ"አንተ እኔን ለአውሬ ጥለህ መክበር ትፈልጋለህ ?"

ጀጎንም ወደ አሩአሳ በፍጥነት ሄደና "አንተ ክፉ ለሱም ነገርከው " ብሎ ሲያንባርቅ

ሙማዚስ ወደ ጓደኛው ዙሮ "ለካስ ባንድ ሁናችሁ በኔ ላይ ስት ዶልቱብኝ ነበር። በቃ ሁላችንም እራሳችንን እናድን " አለ ጀጎን ጠርጥሮ። ስንቁን አንስቶ ከፊት ቀድሞ ሄደ። አሩአሣም የዉሃውን ኮዳ አንስቶ ተከተለው ።

ጀጎንም ለጓደኛው ነገሩን ሊያስረዳው "ስማኝ"

ሙማዚስም "ያልጠረጠረ ተመነጠረ አለ ያገሬ ሰው አልሰማህም አንድ ነገር እንዳታናግረኝ ።" አለውና ወደፊት ተራመደ ሁለቱ ምግብና ውሃ ይዘው ጀጎን በባዶ እጁ ጉዞው ቀጠለ ።

ከረዥም ጉዞ በኋላ ለማረፍ ሲቀመጡ ሙማዙስ ሁለቱን እንደባላንጣ ቆጥሩዋቸው እንብላ ሳይላቸው ሳይላቸው ማእዱን ቆረሰ።

አሩአሣም ውሃውን እየተጎነጨ ተቀመጠ ። ወዲያው ሙማዚስን ምግቡ አነቀው ፍጥጥ ሲል ጓደኛው ጀጎን እየሮጠ ሄዶ ወገቡን መቶ ጉሮሮው ላይ የቆመውን ምግብ አወረደለት አሩአሣ የሚሰሩት ትእይንት ይመስል ይስቃል ።

ጀጎንም ሙማዚስን እያረጋጋ እያለ አሩአሣ መጣና ምግቡን ወስዶ በፍጥነት መብላት ጀመረ በውስጡ እያሰበ ምግቡን ሲውጠው ትናጋው ውስጥ ሂዳ ተሰነቀረች ።

ትንታው ቢያጠቃውም ጀጎን እያየ ዝም አለው ። ምክንያቱም ሁለቱን ሊያጣላቸው ስለነበረ ነው አሩአሣ እያዩት ህይወቱ አለፈ ። ሙማዚስ ስለጥፋቱ "ይቅርታ ታማኙ ጓደኛዬ እኔ አንተን ባለማመኔ አስከፍቼሀለው ።" ሲለው

"አሉባልታ እንኳን እኔና አንተን ይቅርና ሀገርና ሀገርን እስከማፍረስ ይደርሳል ። ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች እከሌ እያሉ ሲነግሩህ አትቀበል ። "

ተባብለው ጉዞዋቸውን ቀጠሉ ። ክፉ ምግባር ዙሮ እስን ነው ። የሚጎዳው "ስራ ለሰሪ ው " አይደል የሚባለው

አክሊሉ ፍስሀ ከበደ(ዘርአልባው ባላገር)