አላባ

አለባ ከጥንት ጀምረው የጋብቻ ስናራስርዓት አለደዕሞ ይበለል

ሀላባ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።

I. የነቀታ ሴራ (የሴራ ማሰልጠኛ ተቋም)   ጥንታዊ ሀላቦች ሀገረ መንግስቱ የሚተዳደርበት ሴራ በሴራ ቅቡልነት ያገኙ የህዝቡ ባህልና ወግ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የዘየዱት ዘዴ ቢኖሮ ታዳጊዎች የህፃንት ዘመናቸውን አጠናቀው ወደ ወጣትነት በሚያደርጉት ሽግግር በየዓመቱ የሰድስት ወር ልምምድና የስልጠና ጊዜ እንዲኖሯቸው ማድረግ ሲሆን ይህም ተቋም የነቀታ ሴራ ተብሎ ይታወቃል፡፡  

ይህም የስልጠና ተቋም ሲሆን ስልጠና የሚሰጠው ከግርዘኝነት ቀጥሎ ባለው 6 ወራት ውስጥ ሲሆን በዚህ ወቅት ግርዘኞች በሀገር መንግስቱ ውስጥ ያለውን የአደረጃጀት አይነትቶችን! የስልጣን ክፍፍሎችን! የዜጎች የስራ ድርሻዎችን! ባህላዊ ክዋኔዎችን! ስነ ጥበቦችን! የሀገሪቱ የሴራ ስረዓቶችን!  የማዕረግ ስሞችን! ጀግና መፍጠሪያ መንገዶችን ባጠቃላይ ሀገረ መንግስቱ ስረዓት እንዴት እንደሚሰራ በመጀመሪያ 3 ወር በቲዎሪ ቀጥሎ ባሉት 3 ወራት ደግሞ በተግባር በጫወታና በሚያዝናና ሁኔታ እንዲሰለጥኑና እንዲለማመዱ የሚደረግበት ተቋም ነው።   

አሁን ላይ የሀላባ ሀገረ መንግስቱ ነባራዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ የተቀየረ በመሆኑ የጥንታዊ ሀላቦች የሀገረ መንግስታቸው መንግስታዊ አሰራር በኢትዮጵያ መዕከላዊ መንግስት ተክቶ የተዳከመ  ቢሆንም ጥንታዊ ሀላቦች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ብለው ታዳጊዎች እንዲማሩበት ያስቀመጡት የሴራ ማሰልጠኛ ተቋም  አሁንም ከኛ ዘመን ድረስ መድረስ ግን ችሏል። ሆኖም ስልጠና የሚሰጠው ከግርዘኝነት የተገናኘ ስለነበር የሀላባ ኦገቴ ባአንድ ወቅት የሴቶች ግርዘት እንዲቀርና ሴቶች ባይገረዙም በክዋኔው እንዲሳተፉ በወነው መሰረት ተሻሽሎ እንደሚከተለው እየተፈጸመ ይገኛል፡፡


  የስልጠናው ሂደት   በሀላባ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር መሰረት "ኢብጂ" ተብለው የሚታወቁ ያልተገረዙ ወንድ ህፃናት  'መሰሮ" ሀምሌ ወር መጀመሪያ ቀኖች ይገረዛሉ። ከተገረዙበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ወራት ከቤት ሳይወጡ እየተመገቡ ! "ገዳሞጂ" ተብለው ከሚታወቁ በቅርብ አመታት ከተገረዡ ልጆችና ከቤተሰቦቻቸው የቲዎሪ ልምድ እየወሰዱ ይቆያሉ።  

"ኢዳራ" (መሰከረም) እና "መሼታ" (ጥቅምት) በአከባቢው በሚገኙ ትላልቅ ዛፍ (ነቀታ) ስር በቲዎሪ ቤት ውስጥ የተማሩትን በአጠቃላይም የህብረሀሰቡን የአኗኗር ብሂል ትውፍታዊ አስተዳደር መዋቅር ! የፆታ ልዩነት መሰረት ያደረጉ ሚናዎችንና የስራ ድርሻዎችን ! ባህላዊ እሴቶችን፣ ባህላዊ ችፈራዎችን፣ ስነግጥሞችን፣ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን፣ የሴራ ደንቦችንንና ህጎችን …ወዘተ በጫወታ መልክ መተግባር ይጀምራሉ።    ከነቀታ ቀጥሎ ባሉት ሁለት ወራት "ከአንቶጎታ" ህዳር እስከ "መንገሳ" ታህሳስ አጋማሽ ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት እየተንቀሳቀሱ "ሀዌሻ" ድግስ እየተመገቡ ሁለተኛውን የተግባር ልምምድ ይወስዳሉ።    እንዲህ እያለ ለስድስት ወራት የተከናወነው ስርዓት ለተሳታፊ ልጆች በእድሜ ዘመናቸው በፍፁም ከማይረሷቸው መልካም አጋጣሚዎች ትዝታዎችና አይረሴ የሕይወት ገጠመኞች መካከል አንዱና ዋነኛ በመሆኑ ግርዘኞች እሄ የደስታና የክብር የስድስት ወር ጊዜ እንዲሁም የልጅነት ጊዜ እንዲያልቅባቸው አይፈልጉም።   ምክኒያቱም ስድስት ወራትን ከፈጀው አስደሳች በጫወታ የታገዘ ክዋኔዎችን ጨርሰው ወደ ወጣትነት ደረጃ ፣ሀላፊነትን ወደ መቀበል የሚሸጋገሩበት የሽግግር ወር ነውና "መንገሳን"  እንዲህ እያሉ ይረግሙታል።    ሀይ መንገሳ  (ወይ ታህሳስ) ሀይ ደለንሳ    (ወይ ችኮላህ)


ሀይ ኦሲማ ኦሮኢማ (ወይ ልጅነት መሄዷ ነው) ኦረተኒ መረሪማ     (ስትሄድ አሳዘነችኝ)   "ወማጉ ባቦቤ" (ወማ ልቡ ባር ባር አለው) "መንገሱ አጎቤ" (መንገሳ ገባኮ)   መንገሲቾ (አንቺ መንገሳ) ወማጊ መሲቾ (የወማ ጠላት)   እያሉ በእንባ እየተራጩ ልብ በሚሰርቅ ዜማ ያዜማሉ።  


መንገሳ የልጆቹን ሀዝን ከቁብ ሳይቆጥር ጉዞውን ይቀጥላል። በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ከህፃንነት ወደ ወጣትነት! ከጫወታ ወደ ኃላፊት እረካብ እያሻገረ ጥንታዊ የሀላባ አባቶች መተግበር ከጀመሩበት ጊዜ ጀመሮ ቀጥሏል።   የመንገሳ መጨረሻ ላይ ግርዘኞች ህፃንነታቸውን ተሰናብተው ለመሻገር ረጅም ዱላ ይዘው አያዜሙ ወደ ገበያ ይሄዳሉ።

ይህ ስነ-ስረዓት "ሁሉቃ" መሻገረ ይባላል። በዚህ ወቅትም ገበያውን እኩል ገምሰው እያለፉ ያዜማሉ።   ወማጎ ኩን ሀንቄከንዶ (ንጉስ ሆይ ይህ እውነት ነው ወይ) ኩ ከምሱ ሁለቃን ከንዶ (ይህ ሀሙስ መሻገሪያ ነው ወይ) ወለቤ ኩን ሀንቄን ከንዶ (ወለቤ ይህ እውነት ነው ወይ) ኩ ከምሱ ሁሉቃን ከንዶ (ይህ ሀሙስ መሻገሪያ ነው ወይ) አድላ ኩን ሀቄንከንዶ (አድላ ይህ እውነት ነው ወይ) ኩ ከምሱ ሁሉቃ ከንዶ (ይህ ሀሙስ መሻገሪያ ነው ወይ)   እያሉ በሀዘን የተሞሉ ዜማዎች እያዜሙ ገበያውን አቋርጠው አልፈው ወንዝ ሄደው ታጥበው ይመጣሉ።

    (ወማ፣ ወለቤ ፣ አድላ በነቀታ ስልጣና ወቅት የሚወስዱት የስም አይነቶች ናቸው፡፡)     ከሁሉቃ ከጥሎ ያለው ክዋኔ ፀጉር መላጨት ነው። ግርዘኝነት የተጣቸውን ስሞችን እየጠሩ "ባንተ ሙጥኝ ብለናል ይህ ፀጉር እንዳይቆረጥብን"እያሉ የሀዘን እንጉርጉሮ ያሰማሉ።   ወማጎ ኪን ተመገኜ (ወማጎ ባንተ ሙጥኝ) ከሲጃ ሜዶኑከኔይህ (ጎፈሬዬ አይላጭብን) ወለቤ ኪን ተመገኜ (ወለቤ ባንተ ሙጥኝ) ከሲጃ ሜዶኑከኔ (ጎፈሬዬ አይላጭብን) አድላ ኪንተ ተመገኜ (አድላ ባንተ ሙጥኝ) ከሲጃ ሜዶኑከኔ (ጎፈሬዬ አይላጭብን)   በማለት ሀዘናቸውን በዜማ ይገልጻሉ ያዜማሉ።

  በመጨረሻም ልጅነታቸውን በመለጨት ወደ ወጣትነት ይገባሉ።የሴራ ስረዓቱን፣ የሴራ አደረጃጀቱን፣ መሪዎችን ማክበር፣ የኦገቴ ወይይት፣ ባህላዊ ጭፈራዎችን ፣ባህላዊ ዜማዎችን፣ ችግሮችን በድርድር መፍታትን፣ስነቃሎችን፣ ፉከራዎችን፣የዜጎች የስራ ድርሻዎችን    መንገሳ ለሀላባ ህዝብ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላ ዘመን መሻገሪያ ሲሆን ለሀላባ ህፃንነት ደግሞ ከህፃንነት ወደ አዋቂነት የሚሻገሩበት ወር ነው።

  1. መንገሳና_ሀላባ

የሀላባ ብሔረሠብ የራሱ የሆነ የወራት አቆጣጠር አለው። ከወራቶች ሁሉ የመጀመሪያ የሆነው #መንገሳ የዘመን መለወጫ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ወር በሀላባ ህዝብ ዘንድ ልዩ ትርጉም አለው። ምክንያቱም ይህ ወር የእፎይታና የመደሰቻ ጊዜ ነውና።

ይህ የመንገሳ ወር በየዓመቱ በታህሳስ ወር የሚከሰት ወር ሲሆን አርሶ አደሩ ለዓመት የለፋበትን አዝመራ ወደየቤቱ የሚያስገባበት፤ ቀድሞ ሰብስቦ የጨረሰው ደግሞ የእፎይታ ጊዜውን የሚያጣጥምበት ወር ነው። በዚህም ምክንያት አርሶ አደሩ #ለመንገሳ ወር ልዩ ቦታ አለው።

መንገሳ ለአዋቂው ብቻም ሳይሆን ለህፃናቱም ልዩ የደስታ ማጣጣሚያና የትዝታ ጊዜ ነው። በተለይ የሀላባ ግርዘኞች መንገሳ ሲመጣ አንድም የሚደሰቱበት አንድም የሚያዝኑበት ሠርግና ምላሽ የሚሆንባቸው ጊዜ ነው።

በተለይ የሀላባ ግርዘኞች ለአራት ወራት እየተዝናኑና የሀላባን ባህላዊ ክዋኔዎች በከፊል እየተለማመዱ የቆዩበትን የግርዘኛነት ህይወት (gadata) የሚያጠናቅቁት በዚሁ መንገሳ ወር ነው።

በዚህ የመንገሳ ወር ከአንድም ሁለት ጊዜ የሀላባ ግርዘኞች ወደሚቀርባቸው ከተማ ለስንብት የጋራ ደስታ (ሁሉቃ) ወጥተው ባህላዊ ትይዕንት የሚያሳዩበት ጊዜ ነው።

ግርዘኞቹ ሁሉቃ ሲወጡ ከተማ ውስጥ ሲንሸራሸሩ ያገኛቸው ተመልካችም የግርዘኞቹ ደስታ ይጋባበታል። አንዳንዱ የራሱን የግርዘኛነት ጊዜን በትውስታ እያሰበ ትናንትን እንደዛሬ በትዝታ ያሳልፋል። መንገሳ የልጅ የአዋቂው የደስታ ጊዜ ነው የሚባለውም ከዚሁ በመነሻ ነው።

የሀላባ ብሔረሰብ ዘመን የማይሽራቸውን ሁሉን አቀፍ ባህሎቹን በቃልና በክዋኔ የሚገልፅበትን "የሴራ" በዓል ከህፃን አስከ አዋቂ በጋራ ወጥቶ የሚያከብረውም በዚሁ የመንገሳ ወር ነው። በዚህ በዓል ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጅና የሀላባ ወዳጅ በጋራ ተሰባስቦ ከቀበሌ እስከዞን በሁሉም የአስተዳደር መዋቅር በማዕከል በተመረጡ ቦታዎች እየተገናኘ በባህላዊ ዕሴቱ የሚደምቅበት ነው።

በህዝባዊ ትዕይንቱ ላይ የሀላባ ባህላዊ ባርኔጣ (ቆሜ)ን ጨምሮ ሌሎች ባህላዊ አልባሳትና ከበዓሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምርቶች በሰፊው የሚመረቱበትና ለገበያ የሚቀርቡበት ጊዜ ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች "ከመቼው በደረሰልን" ብለው የሚጓጉለት ወር ነው መንገሳ።

አብዲረዛቅ ገ/ሁልጋጋ በ/ ጠለሃ

Abdirezak Hulgaga Teleha

ሰኔ -2016 ሀላባ በሸኖ