ኆኅተ ወይም መሰረታዊ የኆኅተ አመክንዮ አይነት ሲሆን ከግቤቶቹ ሁሉ ቢያንስ አንዱ እውነት (1) (ከፍተኛ ቮልት ከሆነ ውጤቱ ምንጊዜም እውነት(1) ይሆናል። ውጤቱ ውሸት (0) የሚሆነው ሁሉም ግቤቶቹ ውሸት (0) (0ቮልት) ሲሆኑ ነው።

ዲጂታል ዑደት
ዲጂታል ዑደት · ኆኅተ አመክንዮ · ዕልፍ ኩነት ማሽን
ግቤት ግቤት
ግቤት A ግቤት B A ወይም B
0 0 0
0 1 1
1 0 1
1 1 1

ይህን ጠባይ በቀላሉ ለማስታወስ በሁለት መልኩ ይቻላል፦ 1) የኆኅተ-ወይም ውጤት ምንጊዜ ከግቤቶቹ ውስጥ ትልቅ ዋጋ ያለውን ግቤት ይከተላል። 2) የኆኅተ-ወይም ውጤት እውነት (1) እሚሆነው ከሁለቱ አንዱ ግቤት ወይንም ሁለቱም እውነት ከሆኑ ነው።

ኆኅተ-ወይም በለት-ተለት ንግግር ወይም የሚባለውን የአመክንዮ መሳሪያ በኤሌክትሪክ አካላት የሚተረጉም እቃ ነው። ለምሳሌ «አበበ ረጅም ነው ወይም አለሚቱ አጭር ናት» ይሄ አረፍተ ነገር አበበ ረጅም ከሆነ ወይንም አለሚቱ አጭር ከሆነች ወይንም ሁለቱም የተባሉትን ሆነው ከተገኙ አጠቃላይ ዓረፍተ ነገሩ እውነት ይሆናል ማለት ነው። ይሄን ተግባር በኤሌክትሪክ ለማስላት የሚረዳ ኆኅት ነው።

 
የኆኅተ አመክንዮ ምልክቶች : ሀ) በማብሪያ ማጥፊያ, ለ) አይ ኢ ሲ ሐ) ብዙ ጊዜ ኆኅተ-ወይም ን የሚወክል ምልክት

በኤሌክትሮኒክ አሰራሩ

ለማስተካከል
 
 
በCMOS የተሰራ ኆኅተ-ወይም