ባህሩ ቀኜኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆኑ ብዙ ባህላዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ። አርቲስት ባህሩ ቀኜ ኢትዮጵያ ውስጥ በማሲንቆ አገራረፋቸውና በድምፃቸው ቃና ከሚታወቁት አንጋፋ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ። አርቲስት ባህሩ በሀገር ውስጥ በአገር ፍቅር ቲያትርና ከሀገር ውጭም በአፍሪካ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ሙያቸውን አቅርበዋል።

የህይወት ታሪክ ለማስተካከል

አርቲስት ባህሩ ቀኜ ቸኮል በሰሜን ወሎ በዋድላ ደላንታ ልዩ ስሙ ወገል ጤና ከተባለው ስፍራ በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. ተወልደው በልጅነት እድሜአቸው በመንፈሳዊ ት/ቤት ገብተው ዳዊት፣ ፀዋተወ ዜማ ተምረዋል። ከቀሰሙት ፀዋተወ ዜማ አኳያ ዝንባሌያቸው ወደ ድምፃዊነት በማምራቱ በወቅቱ ከተወለዱበት አካባቢ በሙያቸው ተመርጠው ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ በአልጋ ወራሽ ቤተ መንግስት ተመድበው በማገልገል በሙያቸው ከፍተኛ ዝና አትርፈዋል።

የስራ ዝርዝር ለማስተካከል

ማጣቀሻዎች ለማስተካከል

  • ባህሩ ቀኜ - ምርጥ ዘፈኖች ቁጥር ሁለት አልበም አውርድ

SamyPlus፣ 2000 (CD)