Open main menu

ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ

የክርስትና ሃይማኖት ፈላስፋ


ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ (በግሪክ: Ἅγιος Βασίλειος ὁ Μέγας, Ágios Basíleios o Mégas) (በእንግሊዘኛ Basil of Ceasarea ሲነበብ ባዚል ኦፍ ሢዛሪያ)በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር ። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ።

ቅዱስ ባስሊዮስ
ከሦስቱ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ
የቄሣርያው ኤጲስ ቆጶስ
ስም ባስሊዮስ ዘቄሣርያ
የአባት ስም ቀዳማዊ ባስልዮስ
የእናት ስም ኤሚልያ
የተወለደው ፫፻፳፩ ወይም ፫፻፳፪ዓ.ም.
ያረፈበት ጥር ፮ ቀን ፫፻፸፩ ዓ.ም. በቀጰዶቂያ
የሚከበረው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

በኦርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን
በኮፕት ቤተክርስቲያን
በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
በአንግሊካን ኮሚዩነን ሉተራኒዝም
የንግሥ በዓል ጥር ፮ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ጄኑዋሪ ፩ና ፴ በቤዛንቲን ክርስቲያን
ጄኑዋሪ ፲፬ በሰርቢያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን
ጄንዋሪ ፪ በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
ታውት ፮ በኮፕት ቤተክርስቲያን

ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል ። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጷቅሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል ።

የቀደመ የሕይወት ታሪኩና ትምህርቱEdit

ባስሊዮስ ከቀዳማዊ ባስሊዮስና ከኤሚልያ የቄሣሪያዋ[1] በ፫፻፳ ዓም አካባቢ በቀጰዶቂያ ተወለደ[2] ። እናትና አባቱ እግዚአአብሔርን በጣም የሚወዱና ጸሎተኞች የነበሩ ሰዎች ነበሩ[3] ። የእናቱ አባት ከቆስጠጢኖስ ፩ኛ በክርስትና ማመን በፊት ሰማዕት ሆኖ ያለፈ ሰው ነበረ[4][5] ። ጸሎተኛ ባልቴቱ ማክሪናም የጎርጎርዮስ ታውማታርገስ (የኒዎ ቄሣርያን ቤተክርስቲያን በአቅራቢያው የመሠረተ)[6] ተከታይ የነበረች ባስሊዎስንና አራቱን ወንድሞቹንና እህቱን ፣ ወጣትዋ ማክሪናናውክራቲየስጴጥሮስ የሰባስቴውንናጎርጎርዮስ የኒሳውን (ወደፊት ታላቅና የተከበሩ ቅዱሳን የሚሆኑ) በክርስትና ሃይማኖት ሥርዐት አሳደገች ።

ባስሊዮስ በቄሣርያ ማዛካ ቀጰዶቂያ በአሁኑ ዘመን አጠራር ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት በ፫፻፵፪ ፵፫ ዓ.ም.አካባቢ ተምሩዋል[7] ። እዛም ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን የረጅም ጊዜ ጉዋደኛ የሚሆነውን ተዋውቋል[8] ። ባስሊዮስና ጎርጎርዮስ አንድላይ በመሆን ለከፍተኛ ትምህርትና በተጨማሪ የሊባኒየስን ትምህርታዊ ንግግር ለማጥናት ወደ ቁስጥጥኒያ አምርተዋል ። ሁለቱ በአቴንስ በ፫፵፪ ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ ለስድስት ዓመት ተቀምጠዋል ። በዛም ቆይታቸው ጁሊያን ዘአፖስቴት ወደፊት ንጉሥ የሚሆን ተማሪ ተዋውቀዋል[9][10] ። ባስሊዮስ አቴንስን በ፫፵፰ ለቆ ወደ ግብፅና ሶርያ ከተጉዋዘ በኋላ አገሩ ቄሣርያ የሕግ ሥራ በመለማመድና የንግግር ችሎታ ሲያስተምር ቆየ[11]

የባስሊዮስ ሕይወት ኢውስታቲየስ የሴባስትን ኃይለኛ የማሳማን ችሎታና ጥሩ ግብረገብ ያለው[12]የተዋወቀ ጊዜ ሕይወቱ ሙሉበሙ ተቀይሩዋል ። ከዚህም የተነሳ ሕጋዊ የማስተማር ሥራውን ትቶ ሕይወቱን ለእግዚአብሔር ሰጠ ። ይህንንም የመንፈሳዊ ሕይወቱን መነቃቃት የሚያሳይ ጽሑፍ እንደሚከተለው አስቀምጦታል ፡

ብዙውን ጊዜዬን በማይረቡ ነገሮች አሳለፍኩ የወጣትነት ዕድሜዬንም በከንቱ ልፋትና እግዚአብሔር ሞኝነት ላደረገው ጥበብ ። በቅጽበት ከኃይለኛ እንቅልፍ ነቃሁ የወንጌልንም እውነተኛ ብርሃን አጥብቄ ያዝኩ የዚህንም ዓለም ንጉሦች ጥበብ ባዶነት ተረዳሁ [13]

ባስሊዮስ በአኔዚEdit

አኔዚEdit

 
የባስሊዮስ ዘቄሣርያ የሩሲያ ምስል

ከተጠመቀ በኋላ ባስሊዮስ በ፫፻፵፱ ዓ ም ወደ ፍልስጤም ፣ ግብፅ ፣ ሶርያ እንዲሁም ሜዞፖታሚያ የመመንኮስንና የገዳማዊነት ትምህርት ለማጥናት ሄደ ።[14][15] ያለውን ሐብት በሙሉ ለድሆች አድሎ እንደጨረሰ ወደ ምነና በፖንተስ ኒዎሢዛርያ (በዘመኑ አጠራር ኒክሳር ቱርክ) ቤተክርስቲያን ገባ ።[14] ባስልዮስ ይህን የገዳማዊ ኑሮ ቢያከብረውም ለሱ እንዳልተጠራ ተረዳ ።[16] የሴባስቴው እዩስታቴየስ እጅግ የታወቀ መኖክሴ በፖንተስ አካባቢ ባስሊዮስን ያስተምረው ነበር ። በዶግማ ላይ ግን ይለያዩ ነበር ።[17]

ይልቁን ባስሊዮስ በመንፈሳዊ ማኅበራዊ ኑሮ ተሳበና በ፫፻፶ በአስተሳሰብ ከእሱ ጋር የሚመሳሰሉትን የክርስትና ደቀመዝሙሮች ወንድሙን ጴጥሮስን ጨምሮ ማሰባሰብ ጀመረ ። አንድላይ ሆነው በቤተሰቡ ርስት ላይ አኔዚ አጠገብ ገዳም መሠረቱ ።[18] በጣም ግልፅ ለማረግ (በዘመኑ አጠራር ሶኑዛ ወይም ኡሉኮይ የዬሲሊርማክ ባሕርና የኬልኪት ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ማለት ነው ።)[19]. ባልተቤትዋ እናቱ ኤሚልያ ፣ እህቱ ማክሪናና ሌሎች ሴቶችም ራሳቸውን ለቅዱስ ተግባር መጽዋት በማድረግ ከባስሊዮስ ጋር ተባበሩ ። (ይህን ማኅበረሰብ የመሠረተችው እህቱ ማክሪና ናት የሚሉም አሉ) ። [20]

ቅዱስ ባስሊዮስ እዚህ ባታ ላይ ስለ ገዳማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ጽፎ ነበር ። ጽሁፉ ግን ለምሥራቃዊ ክርስትና ዕድገት ከፍተኛ ምክኒያት ሆንዋል.[21] በ፫፻፶ዓ ም ባስሊዮስ ጉዋደኛውን ጎርጎሪ (ግሬጎሪ) የናዚያነስን በአኔዚ እዲቀላቀል ጋበዘው። [22] ጎርጎሪዮም (ግሬጎሪ) እንደመጣ በኦሪጄን ፊሎካሊያ የኦሪጄን ሥራዎች ስብስብ ላይ ጥናት ማድረግ ጀመሩ ። [23] ከዚህም በኋላ ግሬጎሪ ወደ ናዚያነስ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ወሰነ ።

ባስሊዮስ የቁንስጥጢናውን የሊቃውንት ጉባዔን ፫፻፶፪ ዓ ም ተሳተፈ ። በመጀመሪ ከኤዩስታቲየስና ከሆሞወሲያንስ ወገነ ፣ ግማሽ አራዊያን የሆነ የመናፍቅ ቡድን ፣ ወልድ ከአብ ጋር ተመሳሳይ እንጂ አንድ ባሕርዪ ወይም አካል አይደለም ብለው ከሚያስተምሩ ጋር ማለት ነው። [24] ሆሞወሲየንስ የአውኖሚየስን አርያኒዝም ይቃወማሉ ግን ደግሞ ከኒቂያ ጉባዔ ተከታዮች ጋር የሥላሴን አንድነት "ሆሞወሲዮስ" ከሚያስተምሩት ጋር መተባበር አይፈቅዱም ። በዚህም ቢሆን በዚያ የባስሊዮስ ጳጳስ ዲያኒየስ የቄሣሪያው የሚከተሉት የቀድሞውን ንቂያ ስምምነት ነበረ ። ባስሊዮስም ወዲያውኑ ሆሞወሲያንስን ጥሎ እንዲየውም ጠንካራ የኒቂያ ጉባዔ ውሳኔን ተከታይ ሆነ ። [24]

ባስሊዮስ በቄሣሪያEdit

ቄሣሪያEdit

 
የሦስቱ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች ምስል: ታላቁ ባስሊዮስ (በግራ) ዮሐንስ አፈወርቅ (በመሐል) እና ግሬጎሪ ቴዎሎጂያኑ (በቀኝ)—ከሊፒ ታሪካዊ ሚይዚየም ሳኖክ ፖላንድ

በ፫፻፶፬ ዓ ም ጳጳሱ ሜለቲየስ የአንጾኪያው ባስሊዮስን ዲያቆን አድርጎ ሾመው ። አውሰቢየስ ደሞ በቄሣሪያ ቤተክርስቲያን በ፫፶፯ ዓ ም ፕሬስቢተር እንዲሆን ሾመው ። እኒህ የቤተክህነት ጥያቄዎች የባስሊዮስን ምርጫ የማይመጣጠኑ ስለሆኑ የሥራውን አቅጣጫ እንዲቀየር አድርገዋል ።[14]

ባስሊዮስና ግሬጎሪ ናዚያነስ ለጥቂት ዓመት የአርያኒዝም መናፍቅ ትምህርት የቀጰዶቂያን ክርስቲያኖች ይከፋፍላል ተብሎ ስለሚያሰጋ ሲታገሉ ቆዩ ። በኋላም የማሳመኛ ንግግር በትልቅ ደረጃ ውድድር (ክርክር) ከታዋቂ አርያውያን ቴዎሎጂየንና ተናጋሪዎች ጋር ለማድረግ ስምምነት አደረጉ ።[25]በንጉሥ ቫሌንስ ተወካዮች መሪነት ከተደረገው ክርክር በኋላም ግሬጎሪና ባስሊዮስ አሸናፊዎች ሆነው ወጡ ። ይህ መሳካት ለግሬጎሪና ለባስሊዮስ የወደፊት ሥራቸው በቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት መሆኑን አረጋገጠላቸው ።[25] ቀጥሎም ባስሊዮስ የቄሣሪያን ከተማ አስተዳደር ወሰደ ።[21] አውሰቢየስ ግን በባስሊዮስ ፈጣን እድገትና በማኅበረሰቡ ባገኘው ተቀባይነት በመቅናት ወደ ነበረበት የገዳም ብቸኝነት ኑሮ እንዲመለስ ፈቀደለት ። ቆይቶ ግሬጎሪ በዚም በዚያም ብሎ ባስሊዮስን እንዲመለስ አሳመነው ። ባስሊዮስም እንዳለው አደረገ በዚያችም ከተማ ለበርካታ ዓመት ውጤታማ አስተዳዳሪ ሆነ የተደነቀበትን ሥራ ሁሉ ለአውሰቢየስ ተወለት ።

በ፫፻፷፪ ዓ ም አውስቢየስም ሞተ ባስሊዮስም እንዲተካው ተመረጠ በዛውም ዓመት የቄሣሪያ ጳጳስ ሆነ ።[26] አዲሱ የቄሣርያ ጳጳስ ሹመቱ በተጨማሪ የፖንተስ ኤክስአርክና የሜትሮፖሊታን ጳጳስ (አምስት ጳጳሳትን የሚያካትት) ሲያስሰጠው ከአምስቱ አብዛኞቹ የአውስቢየስን ቦታ እንዲይዝ የማይፈልጉ ነበሩ ። ይህን ጊዜ ነው የሹመቱን ኃይል ለመጠቀም ያስፈለገው ።

ባስሊዮስ ለሃይማኖቱ የጋለ ስሜት ያለው ፣ ትዛዝ ሰጪ ደግና ለሰው አዛኝ ነበረ ። በዛም ወቅት ድርቅ ባስከተለው ረሐብ ምክኒያት በግሉ ምግብና መጠጥ በማዘጋጀት ለድሆች አድልዋል ፣ ያገኘውን የቤተሰብ ውርሱንም እንደዚሁ ድሆች እንዲጠቀሙ በነበረበት ቤተክርስቲያን አካባቢ አድልዋል ።

ባስሊዮስ ከብዙ የሃይማኖት መሪዎችና ቅዱሳን ጋር ደብዳቤ ተጻጽፍዋል ። ከ ደብዳቤዎቹም መካከል ያለማቋረጥ ሌቦችንና ሴቲኛአዳሪዎችን ለማዳን እንደሠራ የሚያሳዩ ይገኙበታል ። ከሱም ጋር የሚሠሩትን የቤተክህነት አገልጋዮች በሀብት ፍለጋ እንዳይፈተኑ በቀላል የካህን ኑሮ እንዲወሰኑና ብቁ የሆኑ የቤተክህነት ሠራተኞች ለቅዱስ ሥራ እራሱ ይመርጥ እንደነበር ያሳዩ ነበር ። ባለሥልጣኖችንም ፍትሕ ባጉዋደሉ ጊዜ ወይም ግዴታቸውን ባልተወጡ ጊዜ ከመተቸት ወደኋላ አይልም ነበር ። ይህን ሁሉ እያካሄደ በራሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሰፊ ማኅበረሰብ ምዕመናን ጠዋትና ማታ ያስተምርና ይሰብክ ነበር ። ከዚህ በላይ ከተባሉት በተጨማሪ ለብዙ ዓይነት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሆን በቄሣሪያ ባዚሊያድ (Basiliad)[27] የሚባል ሕንፃ ገንብቱዋል ። የሚያካትተውም ለምስኪኖች መኖሪያ ቤት ፣ ወደ መጨረሻ ዕድሜያቸው የደረሱ ሰዎች እንክብካቤ የሚደረግላቸው ቤትና ሐኪም ቤት ናቸው ። ግሬጎሪ ናዚያንዘስ አስተያየት ሲሰጥ የዓለም አስደናቂ ሥራዎች ብሎታል ። [28]

ስለ ሃይማኖቱEdit

ስለ እውነት ያለው ኃይለኛ አቋም በተቀናቃኙ ውስጥ ያለውን ጥሩ ነገር እንዳይታየው አልጋረደውም ፣ ስለሰላምና መታደግ ሲል መስማማት ያለእውነት መስዋትነት የሚገኝ ከሆነ የእውነት መለኪያውን ደስ እያለው አይጠቀምበትም ነበር ። በአንድ ወቅት ንጉሡ ቫሌንስ የአርያን ፍልስፍና ተከታይ የነበረ የመንግሥቱን ተወካይ ሞደስተስን ቢቻል በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከቀሪዎቹ የአርያን ቡድኖች ጋር እንዲስማሙ መልክተኛ አርጎ ወደ ባስሊዮስ ላከው ። የባስሊዮስ ግትር እምቢተኛነት ሞደስተስን "በዚህ ሁኔታ ማንም አናግሮኝ አያውቅም" ብሎ እዲናገር አረገው ። ባስሊዮስም ሲመልስ "ከጳጳስ ጋር ተደራድረህ አታውቅ ይሆናል" ብሎ መለሰለት ። ሞደስተስም ለአለቃው ለንጉሡ "ባስሊዮስ ኃይል እንጂ ሌላ ምንም አይመልሰውም" ብሎ ልኮለታል ። Valens was apparently unwilling to engage in violence. He did however issue orders banishing Basil repeatedly, none of which succeeded. Valens came himself to attend when Basil celebrated the Divine Liturgy on the Feast of the Theophany (Epiphany), and at that time was so impressed by Basil that he donated to him some land for the building of the Basiliad. This interaction helped to define the limits of governmental power over the church.[29]

Basil then had to face the growing spread of Arianism. This belief system, which denied that Christ was consubstantial with the Father, was quickly gaining adherents and was seen by many, particularly those in Alexandria most familiar with it, as posing a threat to the unity of the church.[30] Basil entered into connections with the West, and with the help of Athanasius, he tried to overcome its distrustful attitude toward the Homoiousians. The difficulties had been enhanced by bringing in the question as to the essence of the Holy Spirit. Although Basil advocated objectively the consubstantiality of the Holy Spirit with the Father and the Son, he belonged to those, who, faithful to Eastern tradition, would not allow the predicate homoousios to the former; for this he was reproached as early as 371 by the Orthodox zealots among the monks, and Athanasius defended him. He maintained a relationship with Eustathius despite dogmatic differences.

Basil corresponded with Pope Damasus in the hope of having the Roman bishop condemn heresy wherever found, both East and West. The pope's apparent indifference upset Basil's zeal and he turned around in distress and sadness.

ማጣቀሻEdit

 1. ^ Quasten(1986), p. 204.
 2. ^ Bowersock et al. (1999), p.336
 3. ^ Oratio 43.4, PG 36. 500B, tr. p.30, as presented in Rousseau (1994), p.4.
 4. ^ Davies (1991), p. 12.
 5. ^ Rousseau (1994), p. 4.
 6. ^ Rousseau (1994), p. 12 & p. 4 respectivel
 7. ^ Hildebrand (2007), p. 19.
 8. ^ Norris, Frederick (1997). "Basil of Caesarea". in Ferguson, Everett. The Encyclopedia of Early Christianity (second edition). New York: Garland Press 
 9. ^ Ruether (1969), pp. 19, 25.
 10. ^ Rousseau (1994), pp. 32–40.
 11. ^ Rousseau (1994), p. 1.
 12. ^ Hildebrand (2007), pp. 19–20.
 13. ^ Basil, Ep. 223, 2, as quoted in Quasten (1986), p. 205.
 14. ^ Quasten (1986), p. 205.
 15. ^ Encyclopædia Britannica (15th ed.) vol. 1, p. 938.
 16. ^ Merredith (1995), p. 21.
 17. ^ McSorley, Joseph. "St. Basil the Great." The Catholic Encyclopedia Vol. 2. New York: Robert Appleton Company, 1907. 31 May 2016
 18. ^ Encyclopædia Britannica (15th ed.) vol. 1, p. 938.
 19. ^ mod. Yeşilırmak and Kelkit Çayi rivers, see Rousseau (1994), p. 62.
 20. ^ The New Westminster Dictionary of Church History: The Early, Medieval, and Reformation Eras, vol.1, Westminster John Knox Press, 2008, መለጠፊያ:ISBN, p. 75.
 21. ^ Attwater, Donald and Catherine Rachel John. The Penguin Dictionary of Saints. 3rd edition. New York: Penguin Books, 1993. መለጠፊያ:ISBN.
 22. ^ Rousseau (1994), p. 66.
 23. ^ Merredith (1995), pp. 21–22.
 24. ^ Meredith (1995), p. 22.
 25. ^ McGuckin (2001), p. 143.
 26. ^ Meredith (1995), p. 23
 27. ^ The Living Age. 48. Littell, Son and Company. 1856. p. 326. https://books.google.com/?id=cxAuAAAAYAAJ&lpg=PA326&dq=%22Basiliad%22&pg=PA326#v=onepage&q=%22Basiliad%22&f=false. 
 28. ^ Gregory of Nazianzus. Oration 43: Funeral Oration on the Great S. Basil, Bishop of Cæsarea in Cappadocia. p. 63. http://www.newadvent.org/fathers/310243.htm በ20 February 2016 የተቃኘ. 
 29. ^ Alban Butler; Paul Burns (1995). Butler's Lives of the Saints. 1. A&C Black. p. 14. ISBN 9780860122500. https://books.google.com/?id=XIEAD2MC1YkC&lpg=PA14&dq=%22Basiliad%22%20%22Valens%22%20%22modestus%22&pg=PA14#v=onepage&q=%22Basiliad%22%20%22Valens%22%20%22modestus%22&f=false. 
 30. ^ Foley, O.F.M., Leonard (2003). "St. Basil the Great (329–379)". in McCloskey, O.F.M., Pat (rev.). Saint of the Day: Lives, Lessons and Feasts (5th Revised Edition). Cincinnati, Ohio: St. Anthony Messenger Press. ISBN 978-0-86716-535-7. http://www.americancatholic.org/Features/SaintOfDay/default.asp?id=1248 በ2007-12-15 የተቃኘ.