ሬት (Aloevera) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ወገን ነው።

ሬት

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ለማስተካከል

ደማቅ ቢጫና ቀይ አበቦች አሉት።

ብዙ ዝርያዎች አሉ፤ ከሁሉ የታወቀው Aloe vera ወይም «እውነተኛ ሬት» ነው።ሬት የተለያየ ዝርያ ያለዉ ተክል ሆኖ በብዛ ለዉበት ግብዓቶች መስሪያ አልግሎት ላይ የሚዉል ነዉ፡፡ ይህ የተክል ዝርያ ኢትዮጵያ ዉስጥም በብዛት እንደሚገኝ ይገመታል፡፡ሬት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን አስካሁን ባለዉ ጥናት በጤናዉ ዘርፍና በዉበት መጠበቂያ ኢነዱስተሪዉ ዘርፍ በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ዉስጥ እዚህ ግባ የሚባል አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እንደ ማህረሰብ ለሬት ያለን አረዳድ እና የሚደረገዉ ጥናትም እጅግ አናሳ መሆኑ ነዉ፡፡

አስተዳደግ ለማስተካከል

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር ለማስተካከል

ብዙ ዝርያዎች በኢትዮጵያ አሉ። ለአፍሪካ፣ ማዳጋስካር፣ አረቢያ ኗሪ ናቸው፤ አሁንም ተክሎቹ በተለይም እውነተኛ ሬት የትም አገር ይገኛሉ።

የተክሉ ጥቅም ለማስተካከል

ወፍራም ቅጠሉ ሆድን የምታነጻ መድሃኒት ነው፣ ትኩሳትንም ያቀዝቅዛል፣ የጣፊያና የጉበት ችግሮች፣ የጉልበት ችግሮችም፣ ለማከም ይጠቀማል።

ፈሳሹ ደግሞ ለዓይን ሕክምና ተጠቅሟል። ስለ መራራነቱ እናቶችም ለሕሳናት ጡት ማስወጫ ተጠቅመውታል።

የተከተፈ እሬት በጨው ለፍየልና ለበግ ማለፊያ መኖ ይሠራል።[1]

ውጡም እንደሚያስቀምጥ መድሃኒት ይቆጠራል። በተለይ በአለም ዙሪያ ዕውነተኛ ሬት ለቆዳ ችግሮች እንደ መቃጠሎች እንዲረዳ ይታመናል።

ደባርቅ በተደረገ ባህላዊ ህክምና ጥናት ዘንድ፣ አንድ የኢትዮጵያ ዝርያ A. percrassa የእሬት ሥር ተደቅቆ በማር ተቀላቅሎ ተፍሎም ለ፫ ቀን ለመሳል ይወሰዳል። እንዲሁም የዚህ ዝርያ የቅጠሉ ውጥ ለአህያ ኪንታሮት መታገስ ይለጠፋል።[2]

  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ እስክዳር አበበ - የደባርቅ ባህላዊ ሕክምና 2003 ዓም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ