ሁለት ሞኝ ባልና ሚስት አብረው ይኖሩ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን እንጨት ለቀማ ወደ ጫካ በመንገድ ሲሄዱ፣ ከጫካ የሚመለስ አንድ ሰው አገኙ። ከዚያም እንዲህ ብለው ነገሩት። እዚያ የሚታየው ቤት ውስጥ እንዳትገባ፣ ረሰተን ሳንዘጋ ወጥተን ነው። እቤት ውሰጥ የምንጠቀምባቸውና ያካበትናቸው ነብረቶቻችን በሙሉ በቤት ውስጥ እዳለ ነው። አደራ ወደዚያ ሒደህ ንብረቶቻችንን እዳትነካ ብለው ጉዟቸውን ቀጠሉ። አንጨት ለቅመው ሲመለሱ በቤታቸው ውስጥ ሰባራ ገል እንኳን የሌለበት ባዶ ቤት ሆኖ አገኙት። ብዙም ሳይቆዩ ቀደም ሲል አደራ እዳትነካብን ያሉት ሰው ቤት ውሰጥ ምንም ሳያሰቀር ዘርፏቸው መሔዱን ሲያረጋገጡ፣ ዱላዎቻቸውን በመያዝ ከጫካ ሲመለስ አግኝተውት የነበረውን ሰው መፈለግ ጀመሩ። ከብዙ ፍለጋ በኋላ ስለደከማቸው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በመንገድ ላይ ሌላ ሰው አገኙ። ያገኙትን ሰው አስቁመው በል የወሰድኸውን ንብረታችንን አሁኑኑ መልስ፣ አለበለዚያ በምታየው በያዝነው ዱላ ቀጥቅጠን እንገድልኻለን ሲሉት፣ ሰዎቹ ስለምን ንብረት እንደምታወሩ አልገባኝም፣ ከገበያ የገዛሁነትን ዕቃ ወደሱቄ አድርሼ ከብቶቼን ለማምጣት ወደ ሜዳው እየወረድሁ ነው። ሲላቸው ጭራሽ ወደሱቅህ ወስደህ ልትቸበችብልን ነው፣ እያሉ በያዙት ዱላ ቀጥቅጠው ገደሉት። ይባላል። [ተሻሻሎ ተፃፈ - ማማሩ በዛብህ - ሚያዚያ/2014 ዓ.ም.]

[መደብ:የኢትዮጵያ ቀልዶች]