ለማንነትህ ትርጉም ይኑርህ እኔ ቆይ ማን ነኝ። እኔ እኮ ምንም የማልጠቅም ከንቱ ፍጡር ነኝ። ለምን ተፈጠርኩ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ፈጣሪዬ ሆይ ውሰደኝ ።የሚሉ ሰዎች ለማንነታቸው ፈፅሞ ትርጉም ያጡ ሰዎች ናቸው ። ወደ ፈጣሪ ማቃናት የኢትዮያም ሆነ የኢትዮጵያውያን ባህላችን ነው። ወደ ፈጣሪ መጮህና ማማረር በጣም የተለያዩ ናቸው። ወደ ፈጣሪ መጮህ ማለት አንድን ነገር ለፈጣሪ መንገር ሲሆን ማማረር ግን ከፈጣሪ ጋር እስከመጣላት ሁላ የሚያደርስ መጥፎ ምግባር ነው። ስለዚህ እኔ የተፈጠርኩት ለዚህች ምድር ታላቅ ገፀ በረከት በውስጤ ከተተከለ በኋላ ነው ። ብለን በማመን የሌለንን ከመፈለግ እኔ ምን አለኝ ብሎ ባለን ነገር ላይ መደሰት መቻል አለብን ማለት ነው።

ማወቅን አውቃለው ብዙ ተምሪያለው

ማንም ይበልጠኛል ማንንም በልጣለው።