2 ነቢሪራው ምናልባት በላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1614 ዓክልበ. ያሕል የገዛ ፈርዖን ነበረ።

2 ነቢሪራው ?
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1613 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 1 ነቢሪራው
ተከታይ ሰመንሬ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

ታሪካዊ ሕሊናው ምንም አልተረጋገጠም። ስሙ የሚገኝ በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ብቻ ነው። ከ1 ነቢሪራው ወይም «ነቢራውሬ» ቀጥሎ ሁለተኛው «ነቢራውሬ» ወይም «ነቢታውሬ» አለው። ስለዚህ ለአጭር ጊዜ ከነገሡት ፈርዖኖች መካከል እንደ ሆነ ይገመታል።

በተጨማሪ ከዚያ 1500 ዓመት በኋላ በ150 ዓክልበ. ያህል የተሠራ አንድ ጣኦት ምስል ይታወቃል፤ በመሠረቱ በየጎኑ «ያለፉት ፈርዖን ሰዋጀንሬ»፣ «ያለፉት ፈርዖን ነፈርካሬ»፣ «አህሞስ»ና «ቢንፑ» ይጠቀሳል። በአንድ መላ ምት፣ ከጥንታዊ ምስል ተቀድቶ ፈርዖን ነቢሪራው ሰዋጀንሬ፣ ልጁም 2 ነቢሪራው ነፈርካሬ፣ እና በዘመኑ የኖሩት ልዑላን መስፍኖች አህሞስና ቢንፑ ይጠቀሳሉ። በዚህ አስተሳሰብ «ነፈርካሬ» ሲል የዚህ 2 ነቢሪራው ሌላ ስም ሊሆን ይችላል። ሆኖም የ2 ነቢሪራው ስም በቶሪኖ ቀኖና ብቻ ስለሚገኝ ሌላ ስሙ አይታወቅለትም።

ቀዳሚው
1 ነቢሪራው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1613 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰመንሬ