2 ሐንቲሊ ምናልባት ከ1478 እስከ 1473 ዓክልበ ድረስ ዓክልበ. አካባቢ ከአባቱ አሉዋምና በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ ነበር።

ንጉሥ አሉዋምና ለወራሹ ልጅ ለሐንቲሊ የመሬት ርስት የሚሰጥበት ሰነድ ተገኝቷል። እናቱም ንግሥት ሐራፕሼኪ ነበረች። የሐንቲሊም ኩኔይፎርም ማኅተም ይታወቃል። ወንድሙ ሐሹዊሊ የንጉሣዊ ዘበኞች አለቃና የተከታዩ የ2 ዚዳንታ አባት እንደ ነበር ይታመናል።

በዚህ ዘመን እንደገና የወዳጅነትና ስምምነት ውል ከጎረቤቱ አገር ከኪዙዋትና ጋራ ከንጉሡም ፓዳቲሹ ጋር ተዋዋለ።

ቀዳሚው
አሉዋምና
ሐቲ ንጉሥ
1478-1473 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ዚዳንታ