ፍያካ ኬንፊናንአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ፍያካ የስታርን ልጅ፣ ስታርንም የሩድራይግ ማክ ዴላ ልጅ ነበረ።

የዴላ አምስት ልጆች አይርላንድን ለ፲፪ ዓመታት ገዝተው የሩድራይግ ልጅ-ልጅ ፍያካ መጨረሻውን ከዴላ ልጆች ሴንጋንን ገልብጦ ፍያካ ንጉሥነቱን ከእርሱ ቃመ። ነገር ግን ከአምስት አመት በኋላ ፍያካ በፈንታው በጌናን ማክ ዴላ ልጅ በሪናል እጅ ወድቆ ተገልብጦ ሪናል የዛኔ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘበት።

የፍያካ ማክ ስታርን መጠሪያ «ኬንፊናን» ትርጉም «ነጭ ራስ» ሲሆን፣ ሌቦር ገባላ ኤረን («የአይርላንድ ወረራዎች መጽሐፍ»፣ 1100 ዓ.ም. ግድም) እንዲህ ያብራራል፦ «በእርሱ ፊት የአይርላንድ ከብት ሁሉ ባለ ነጭ ራስ ያለ ነውርም ነበሩ»። ቢባልም በ1625 ዓ.ም. አካባቢ የታተመው የሴጥሩን ኬቲን ታሪክ መጽሐፍ የአይርላንድ ታሪክ ኢንዲህ ይለዋል፦ «በዘመኑ በአይርላንድ ሰዎች ላይ ነጭ ራሶች (ጽጉር) ነበር።»

ቀዳሚው
ሴንጋን
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1525-1520 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሪናል