ፍርዝቢ ውይም በራሪ ዲስክ የሚወረወር የፕላስቲክ ጨወታ ነው። በቅርጹ ምክንያት ዲስኩ ሲወረወር በፍጥነት እየተሽከረከረ ይበርራል። በመጣሉና በመያዙ ብዙ የጨወታና የስፖርት አይነቶች ይወደዳሉ።

ዩኒቨርሲቲ ተማሮች በካናዳ አገር ፍርዝቢ ሲጫወቱ
አንድ ፍርዝቢ

ፍርዝቢ መጀመርያ ባለፈው ክፍለዘመን ዘመናዊ ሆነ። በ1930 ዓም በካሊፎርኒያ ውቅያኖስ ዳር ፍሬድ ሞሪሦን የተባለ አሜሪካዊ ሰው የፈንዲሻ ቆርቆሮ ክዳን ከእጮኛው ጋራ እርስ በርስ ይወራወሩ ነበር። ከትንሽ በኋላ ክብ የኬክ መጥበሻ ከፈንዲሻ ክዳን ይልቅ መወርወሩን አገኙ እና በውቅያኖስ ዳር ላይ «በራሪ ኬክ ድስት» ይሸጡ ጀመር።

ሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ በኋላ በ1938 ዓም ሞሪሦን «ውርሎ-ወይ» የሚባል የፕላስቲክ በራሪ ጨዋታ ነደፈ። በ1940 ዓም «ፍላይን ሶሰር» ተብሎ ይሠራ ጀመር፣ ብዙ ግን አልሸጡም። በ1947 ዓም ሞሪሦኖች የተሻለ ንድፍ «ፕሉቶ ፕላተር» ተብሎ አወጡ።

በ1949 ዓም ዋም-ኦ የሚባል ጨዋታ ድርጅት መብቶቹን ገዙ። በኒው ኢንግላንድ አቅራቢያ ደግሞ ወጣቶች እንዳጋጣሚ የፍርዝቢ ሳንቡሳ ድርጅት ቆርቆሮች ይወረወሩ ነበር። በጨወታቸው ሲወረወሩ «ፍርዝቢ» ብለው ይጮሁ ነበር፤ ዲስኩንም «ፍርዝቢ» ስላሉት የዋም-ኦ ፕላስቲክ «ፕሉቶ ፕላተር» ደግሞ «ፍርዝቢ"" ይሉት ነበር። ስለዚህ፣ በ1949 ዓም የ«ፕሉቶ ፕላተር» ስም በይፋ «ፍርዝቢ» ሆነ። በ1956 ዓም ኤድዋርድ ኸድሪክ ንድፉን እንደገና አሻሸለ።

ዛሬ የ«ፍርዝቢ» ስም በትክክል የዋም-ኦ ድርጅት መብት ቢባልም፣ እንዲህ የሚመስል የሌላ ድርጅት ተወርዋሪ ፕላስቲክ ዲስኮች በጠቅላላ «ፍርዝቢ» በመባል ታውቀዋል።