ጌታቸው ኃይሌ

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

ጌታቸው ኃይሌኢትዮጵያ ደራሲና የግዕዝ ቋንቋ ምሁር ናቸው።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (Getatchew Haile) ሃገራችን ኢትዮጵያ ከኣሏት የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እና ምሁራን ዋንኛው የሆኑና ታላቅ የሃገር ባለውለታ ናቸው። በግዕዝ ቋንቋችን ዙሪያም የበርካታ መጻሕፍት ደራሲ ናቸው። የግዕዝ ቋንቋን በልጅነት ዕድሜኣቸው በተለምዶ የቄስ ትምህርት ቤት ከሚባለው በመጀመር እስከ ኣሁን ድረስ እየተጠቀሙበትና የእዚህን ብርቅ ቋንቋ ታሪክ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እጅግ ከፍተኛ ኣስተዋፅዖ እያደረጉ ያሉ ምሁር ናቸው።

ከ1945 እስከ 1951 ዓ.ም. ኣዲስ ኣበባ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት ከተማሩ በኋላ በ1952 ወደ ግብፅ ሄደው በካይሮ ከተማ ኖረዋል። በ1957 ዓ.ም. ካይሮ ከሚገኘው የኮፕቲክ ቲዎሎጂካል ኮሌጅ (Coptic Theological College) በቢ.ዲ. (B.D) እንዲሁም ከኣሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ኢን ካይሮ (American University in Cairo) በቢ.ኤ. (B.A.) ተመርቀዋል። በመቀጠልም ወደ ጀርመን ሃገር በመሄድ ከኤበርታርድ ካሪስ ዩኒቨርሲቲ (Eberthard-Karis University) በ1962 ዓ.ም. በሴሚቲክ ፍልስፍና በፒ. ኤች. ዲ. (PHD) ተመርቀዋል። በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለኣስር ዓመታት ኣስተምረዋል።

ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ ከ18 በላይ መጻህፍትን ደርሰዋል። ብዙ መጻሕፍትንና ጽሑፎችንም ተርጕመዋል። እጅግ ኣድካሚ የሆነውን፣ ነገር ግን የሃገር ቅርስን በሥርዓት ለማቆየት የሚያስችለውን የኢትዮጵያን ካታሎግ ማኑስክሪፕት ኣዘጋጅተው በማይክሮፊልም በማድረግ ኣዲስ ኣበባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ማኑስክሪፕት ቤተ-መጻሕፍት እና ኮሌጅቪል፣ ማይነሶታ ለሚገኘው ለHill Monastic Manuscript Library ኣበርክተዋል።

ከመጀመሪያ ሥራዎቻቸውም በ1965 ዓ.ም. ወደ ኣማርኛ የተረጐሙት የማርክ ትዌይን (Mark Twain) ኣጫጭር ታሪኮች ኤክስትራክትስ ፍሮም ኣዳምስ ዲያሪ (Extracts from Adam’s Diary) የተባለው ነው። ስለ ታዋቂው የጎንዳጎንዳው ኣባ እስጢፋኖስ በ2006 እና በ2011 በኣሉ ሁለት ጥራዝ መጻሕትን ጽፈዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው በትርጕም ሥራዎቻቸው የሚጠቀሙባቸው ቋንቋዎች፣ የኣማርኛ፣ ግዕዝ፣ ኣረብኛ፣ ሂብሩ፣ ላቲን፣ ግሪክ፣ ጀርመንና ኮፕቲክ ናቸው። የግዕዝ ቋንቋን በተመለከተ በርካታ ሥራዎችን በመሥራታቸው ብዙ ሽልማቶችንና ዕውቅናን ኣግኝተዋል። በበርካታ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ንግግሮችን (lectures) ሰጥተዋል። ግዕዝን ኣስመልክቶ በብዙ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ቃለ ምልልሶችም ተሳትፈዋል።

በግዕዝ ቋንቋ ላይ ለኣበረከቱት ኣስተዋጽዖ የማካርተር ፌሎውስ ፕሮግራም ጂኒየስ ኣዋርድ እና የኤድዋርድ ኡሌንዶርፍ ሜዳል ከካውንስል ኦፍ ዘ ብሪቲሽ ኣካደሚ (MacArthur Fellows Program "genius" award and the Edward Ullendorff Medal from the Council of the British Academy) ኣግኝተዋል።

የዘመናዊ እና የጥንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ-ጽጹፍ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ ያደረጓቸው ምርምሮችና ያሳተሟቸው ጽሁፎች የኢትዮጵያንና የሩቅ ምሥራቅ የክርስቲያን ኃይማኖትን ወጎችን እና ታሪኮችን በማቆየት ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። በቅርቡ ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት ኮሌጅቪል፣ ሚነሶታ በሚገኘው የሴይንት ጆንስ ዩኒቨርሲቲ Regents Professor of Medieval Studies and Cataloguer of Oriental Manuscripts of the Hill Monastic Manuscript Library በመሆን ሠርተዋል። ከ5000 በላይ ማኑስክሪፕቶችን ካታሎግ በማድረግ የግዕዝን ማኑስክሪፕት በማይክሮፊልም በማስረዳት ኣስር ካታሎጎችን ኣሳትመዋል። ይህም ምኑም ሳይጓደል በኢትዮጵያ ብቻ የተገኘውን የሄኖክ መጽሐፍን Book of Enoch ይጨምራል። በእውነቱ ይህ እጅግ ከባድ ሥራ ነው።

ሽልማቶች [edit]

Ethiopic Foundation Award, December 20, 2020. Abebe Bikila’s Life Time Achievement Award, 2018 Honoree of a festschrift volume in 2017: Studies in Ethiopian Languages, Literature, and History Festschrift for Getatchew Haile Presented by his Friends and Colleagues. Council of the British Academy, Edward Ullendorff Medal 2014, awarded for scholarly distinction and achievements in the field of Semitic languages or Ethiopian studies. Ethiopia Diaspora organizations’ recognition for community service, May 26, 1996; November 9, 1996; May 26, 2001; and August 21, 2004. Corresponding Fellow of the British Academy, 1987–present. MacArthur Fellows Program, John D. and Catherine T. MacArthur Fellowship, 1988-1993. Member, Ethiopian Parliament, representing the province of Shoa, 1974-75.


የውጭ ማያያዣዎች ለማስተካከል