ደም በአብዛሀኛው የቀይ ቀለም ያለው የአካል ፈሳሽ ሲሆን በተለያዩ የአካል ክፍሎች በመሰራጨት ለህዋሳት ምግብ እና ኦክስጅን ያደርሳል። እንዲሁም ከእነዚሁ ህዋሳት ፅዳጅ (ዝቃጭ) ያስወግዳል። በደም ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ አይነት ሴሎች ይገኛሉ፤ ነገር ግን በጥቅሉ ነጭ እና ቀይ የደም ሴሎች ብለን እንከፍላቸዋለን። ቀዩ ኦክስጅንን ለሰውነታችን ህዋሶች ሲያደርስ፣ ነጩ የደም ህዋሰ (ሴል) ደግሞ በሽታ አምጪ ተዋስያን ሰውነታችን ገብተው ለበሽታ እንዳያጋልጡን ይከላክሉልናል።