የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (አፍሪካንስ፡ Suid-Afrikaanse nasionale sokker span ስዊድ-አፍሪካንስ ናሲዮናል ሶከር ስፓን) ወይም ባፋና ባፋና ደቡብ አፍሪካን ወክሎ በእግር ኳስ ይወዳደራል። አስተዳዳሪው አካል የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ሲሆን መቀመጫው ሶከር ሲቲ ነው። በአሁኑ ጊዜ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ ሲሆን አምበሉ ደግሞ ስቲቨን ፒየናር ነው። በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ምክንያት ከ1992 እ.ኤ.አ. በፊት ቡድኑ በፊፋ ማዕቀብ ተጥሎበት ነበር። በ2010 እ.ኤ.አ. ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ አገር ስትሆን፣ የቡድኑ ሲፊዌ ሻባላላ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አግብቷል። የቡድኑ ትልቅ ድል በ1996 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫን ማግኘቱ ነው።

ብሔራዊ ቡድኑ በ2008 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ዋንጫ ሲሟሟቅ

ታሪክ ለማስተካከል

እግር ኳስ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የታወቀው በ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ቅኝ ገዢነት አማካኝነት ነው። በአገሩ የነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ፬ በዘር የተለያዩ የእግር ኳስ ማህበራት እንዲኖሩ አድርጓል።

ደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያግብፅ እና ሱዳን ጋር በመሆን የፊፋን 1953 እ.ኤ.አ. ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል። በዚህም ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ሀገራት በፊፋ ውክልና እንዲያገኙ ጠይቀዋል። በዚህም የተነሳ በ1956 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ተመስርቷል።

የአሁን ተጫዋቾች ለማስተካከል

፳፫ ተጫዋቾችን ያቀፈ ቡድን በግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ከግብፅ ጋር ለሚደረገው የ2012 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ማጣሪያ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም ፬ ሌላ ተጫዋቾች ለምልከታ ተጠርተዋል።

ጨዋታዎችና ጎሎች እስከ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ድረስ ትክክል ናቸው።

ቁጥር ቦታ ተጫዋች የትውልድ ቀን ጨዋታዎች ጎሎች ክለብ
በረኛ ዌይን ሳንዲላንድስ ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. 0 0   ማሜሎዲ ሰንዳውንስ
ተከላካይ ሞርጋን ጉድ መጋቢት ፲፬ ቀን ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. 13 0   ሱፐርስፖርት ዩናይትድ
ተከላካይ ሲያንዳ ኩሉ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. 0 0   ማሜሎዲ ሰንዳውንስ
ተከላካይ ሙሎሞዋንዳው ማቶሆ የካቲት ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0   ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
ተከላካይ ፕሪንስ ህሌላ ግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. 0 0   ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
ተከላካይ ምዙቩኪሌ ቶም ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. 1 0   ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ሲያንዳ ዝዋኔ ግንቦት ፳፮ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0   ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ሲያቦንጋ ሳንግዌኒ መስከረም ፲፱ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. 5 1   ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ቴፉ ማሻማይቴ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0   ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አከፋፋይ ህሎምፎ ኬካና ግንቦት ፲፭ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0   ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
አከፋፋይ ታንዱዪሴ ኩቦኒ ግንቦት ፲፬ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 10 0   ጎልደን አሮውስ
አከፋፋይ ታንዳኒ ንትሹማዬሎ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0   ሱፐርስፖርት ዩናይትድ
አከፋፋይ ታቦ ማትላባ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 0 0   ፍሪ ስቴት ስታርስ
አከፋፋይ ኧርዊን ኢሳክስ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. 0 0   ሳንቶስ
አከፋፋይ ሲፊሶ ምየኒ ሰኔ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 0 0   ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ በርናርድ ፓርከር መጋቢት ፯ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 35 10   ፓንሴራይኮስ
ተከላካይ ቩዪሲሌ ዋና ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0   ሳንቶስ
አከፋፋይ ሌህሎሆኖሎ ማጆሮ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 0 0   አማዙሉ
አጥቂ ካትሌጎ ምፌላ ኅዳር ፳ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 38 19   ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ተጨማሪ ተጫዎቾች ለማስተካከል

ቁጥር ቦታ ተጫዋች የትውልድ ቀን ጨዋታዎች ጎሎች ክለብ
ተከላካይ ፑንች ማሴናሜላ ጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. 0 0   ካይዘር ቺፍስ
አከፋፋይ ሲፊሶ ምየኒ ሰኔ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 1 0   ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ ቦንጎልዌቱ ጃዪያ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0   ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ ከርሚት ኢራስመስ ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 1 0   ሱፐርስፖርት ዩናይትድ