የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409

በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት ወደ አዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አየር ዠበብ፣ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።

የአውሮፕላኑ ምስል

አየር ዠበቡ የቦይንግ ፯፻፴፯ ፰-ኤኤስ ሲሆን[1] በጠቅላላው ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ነበር። በአደጋው ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸው አልፏል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።


ይዩ ለማስተካከል

ማጣቀሻ ለማስተካከል

ድር ጣቢያ ለማስተካከል