የቶሪኖ ከፈን ወይም መከፈኛ ጨርቅ የተሰቀለ ሰው ምስል የሚታይበት ጥንታዊ በፍታ ነው። ዛሬ የሚገኘው በቶሪኖ ጣልያ ባለበት ቤተ ክርስትያን በመሆኑ «የቶሪኖ ከፈን» ይባላል። ይሄው በፍታ በመቃብር ውስጥ ሲቆይ ኢየሱስ ክርስቶስን የከፈነው እንደሆነ በሱም ላይ ምስሉ በተአምር እንደተቀረጸ የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም። ሌሎች ግን የጥርጣሬ ባሕርይ ይዘው ይህን ሳይቀበሉ በሰው ልጅ ሰዓሊነት እንደ ተፈጠረ ባዮች ናቸው። ስለዚህ ከበፍታው የተነሣ ብዙ ክርክሮች ሲደረጉበት ውለዋል።

በከፈኑ ላይ ያለው መልክ፣ ቀለሞቹ ሲገለበጡ የፎቶ ኔጋቲቭ መሆኑ ይገለጻል

ከሁሉ የሚያስገርመው ዕድሜው ካሜራ ወይም ፎቶ የማንሣት ዕውቀት መቸም ከኖረ ምናልባት ወደ 1800 ዓመታት በፊት የሚጠጋው ምስል እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ በመሆኑ ሲሆን፡ ምስሉ መጀመርያ በግልጽ የታየበት ወቅት በግንቦት 21 ቀን 1890 ዓ.ም. ሴኮንዶ ፒያ የተባለ አንድ የፎቶ አንሺ ፎቶውን ካነሣ በኋላ ያነሣው ፎቶ በታጠበ ጊዜ ኔጋቲቩን አይቶ በዚያን ጊዜ ምስሉ እራሱ የፎቶ ኔጋቲቭ እንደሆነ ተረዳ። ከ1818 ዓ/ም አስቀድሞ ስለ ፎቶ ኔጋቲቭ ምንም ዕውቀት አለመኖሩ እርግጠኛ ነው። ሆኖም ይህ በፍታ በታሪክ መዝገብ ቢያንስ ከ1349 ዓ.ም. መገኘቱ ደግሞ እርግጠኛ ነው። ስለዚህ ምስሉን በተመለከተ በቀላል የማይመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ቀርተዋል።

ደግሞ ይዩ፦ የጄኖቫ ቅዱስ መልክ