የቢራቢሮ ክፍለመደብ (Lepidoptera) እጅግ ሰፊ የሦስት አጽቄ ክፍለመደብ ነው። ብዙ ዝርያዎች ለቁንጅናቸው ታውቀዋል።

«ንጉሥ ቢራቢሮ» እና «ጨረቃ ብል»
አባ ጨጓሬ - የቢራቢሮ ሕጻን

ከበርካታ ዝርያዎቹ መካከል ብዙዎች ልብስን የሚበሉ አይነቶች ብል ይባላሉ። ሌሎች ቢራቢሮ ይባላሉ።

ቢራቢሮ በሕጻንነቱ በፍጹም የተለየ መልክ አለው፣ ይህም አባ ጨጓሬ ይባላል። እንደ አካለ መጠን ቢራቢሮ ከመሆኑ በፊት ምንም ክንፍ ወይም በረራ የለውም። ከጊዜ በኋላ አባ ጨጓሬ ሲያድግ በልቃቂት ወይም በምድር ተደብቆ ሙሽሬ ይሆናል፤ በኋላም ከዚህ ልቃቂት ወጥቶ አካለ መጠን የሚበርር ቢራቢሮ ነው።