ዚካ ትኩሳት፣ እንዲሁም የዚካ ቫይረስ በሽታተብሎ የሚጠራው፣ በዚካ ቫይረስ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ [1] ምልክቶቹ ከ ከቆላ ንዳድ ጋር ይመሳሰላሉ፡፡ [1] ከ (60–80%) የሚሆነው ታማሚ ምልክት የለውም፡፡ [2] ምልክቶቹ በሚከሰቱ ጊዜ በአብዛኛው በትኩሳት፣ የአይን መቅላት, የመገጣጠሚያ ህመም፣ ራስምታትና በቆዳ ሽፍታስር ይጠቃለላሉ፡፡ [3][1] በአጠቃላይ ምልክቶቹ ቀለል ያሉና ቆይታቸውም ከአምስት ቀናት ያነሰ ነው፡፡ [4] በሽታው በ2015 በጀመረ ጊዜ የደረሰ ሞት አልነበረም፡፡[2] በሽታው ከ ከጡንቻ መዛል ህመም ጋር ግንኙነት አለው፡፡ [2]

ዚካ ትኩሳት
Classification and external resources

አሌክስስ ሳልቫዶር ዚካ ቫይረስ
ICD-10 U06.9 Code change from 21 December 2015
ICD-9 066.3


መንስኤና ምርመራ ለማስተካከል

የዚካ ትኩሳት በዋነኛነት የሚሰራጨው በ ቢንቢ ንክሻ ሲሆን እሱም ከ ኤደስ ስር ይመደባል፡፡ [4] በግብረስጋ ግንኙነትና በደም ንክኪም የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ [4] በሽታው ከ በፅንስ ወቅት ከእናት-ወደ-ልጅ የሚተላለፍ ተሰራጭቶ በሚወለደው ልጅ ላይ ከመደበኛው ያነሰ የራስ ቅል እንዲሀኖረው ሊያደርግ ይችላል፡፡ [1][2] አንድ ሰው ሲታመም በምርመራ የቫይረሱን አር.ኤን.ኤለማወቅ የደም፣ ሽንት ወይም ምራቅ ናሙና ተወስዶ ይመረመራል፡፡ [4][1]

መከላከያና ህክምና ለማስተካከል

በሽታው በተከሰተበት አካባቢ የቢንቢ ንክሻውን ለመቀነስ የቅድመ መከላል መደረግ ይኖርበታል፡፡ [4] ጥረቶቹም ነፍሳት ማባረሪያ፣ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል በልብስ መሸፈን፣ አጎበር፣ የረጋ ውሃ ለቢንቢ መራቢያ ምቹ ስለሚሆን እሱን ማድረቅ፡፡ [1] ውጤታማ የሆነ ክትባት አልተገኘለትም፡፡ [4] በ2015 የብራዚል የጤና ተጠሪዎች እንሚመክሩት ለማርገዝ እቅድ ላላቸው ወላጆችና እርጉዝ የሆነች ሴት በሽታው ስርጭት በስፋት ወደታየበት ቦታ እንዳትሄድ ይመክራሉ፡፡ [5][4] ለህመሙ የተለየ የሕክምና አይነት ባይኖርም የትኩሳት ማስታገሻ መድሐኒት ህመሙ በሚኖር ጊዜ ለመርት ያስችላል፡፡ [4] ሆስፒታል መመዝገብ የሚያስፈልገው አልፎ አልፎ ነው፡፡ [2]

የበሽታ አመጣጥ ጥናት ለማስተካከል

ለበሽታው መነሻ የሚሆነው ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየው በ 1947 ነው፡፡ [6] በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በ በማክሮኔዢያ ፌደራል ስቴት በሚገኙ ህዝቦች መሀል በ2007 ላይ ነው፡፡ [4] በ2016 በ አሜሪካ ክልል ባሉ ሀያ ሀገራት ላይ ተከስቷል፡፡ [4] እንዲሁም በአፍሪካ፣ እስያና ፓስፊክ አካባቢ መከሰቱ ታውቋል፡፡ [1] በ2015 በብራዚል በጀመረው ስርጭት፣ የ አለም ጤና ድርጅትአለማቀፋዊ የአስቸኳይ ጊዜ የማህበረሰብ ጤና ትኩረት አውጇል፡፡ [7]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ "Zika virus" (January 2016). በ3 February 2016 የተወሰደ.
  2. ^ "Factsheet for health professionals". በ22 December 2015 የተወሰደ.
  3. ^ Musso, D.; Nilles, E.J.; Cao-Lormeau, V.-M. (2014). "Rapid spread of emerging Zika virus in the Pacific area". Clinical Microbiology and Infection 20 (10): O595–6. doi:10.1111/1469-0691.12707. PMID 24909208. http://linkinghub.elsevier.com/retrieve/pii/S1198743X1465391X. 
  4. ^ Chen, LH; Hamer, DH (2 February 2016). "Zika Virus: Rapid Spread in the Western Hemisphere.". Annals of internal medicine. PMID 26832396. http://annals.org/article.aspx?articleid=2486362. 
  5. ^ "Brazil warns against pregnancy due to spreading virus - CNN.com". በ24 December 2015 የተወሰደ.
  6. ^ Haddow, AD; Schuh, AJ; Yasuda, CY; Kasper, MR; Heang, V; Huy, R; Guzman, H; Tesh, RB et al. (2012). "Genetic characterization of Zika virus strains: geographic expansion of the Asian lineage.". PLoS neglected tropical diseases 6 (2): e1477. PMID 22389730. 
  7. ^ "WHO Director-General summarizes the outcome of the Emergency Committee regarding clusters of microcephaly and Guillain-Barré syndrome" (1 February 2016). በ3 February 2016 የተወሰደ.