ዊል ስሚዝ (እንግሊዝኛ: Will Smith) (የተወለደው ሴፕቴምበር 25 እ.አ.አ. 1968) የአሜሪካ ታዋቂ የፊልም ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ (ራፐር) እንዲሁም የፊልም ፕሮዲዩሰር ነው። ስሚዝ የአሁኗን ባለቤቱን ፒንኬት ስሚዝን በእ.አ.አ.1997 አግብቶ ጃደን ስሚዝ እና ዊሎው ስሚዝ የሚባሉ ሁለት ወንድ እና ሴት ልጆችን ወልደዋል። ካልቭን ሀርስ

ስሚዝ በሜይ 2010 እ.አ.አ.

ዊል ስሚዝ በመጋቢት 27 2022 ዓም በተደረገው 94ተኛው የአካዳሚ ሽልማት ዝግጅት ላይ ኮሜድያን ክሪስ ሮክ ስለ ባለቤቱ ፀጉር ቀልደሃል በማለት በጥፊ መቶታል። ሮክ የስሚዝ ባለቤት የወነችው ጄዳ ፓንኬት ስሚዝ ፀጉር ከ1997 በተሰራው ጂአይይ ጄን የተሰኘውን የፊልሙን እንስት ገፀ ባህሪ ጋር በማነፃፅር ንብረት ስሚዝን ያስቆጣው። የስሚዝ አፀፋ በአካዳሚውም ሆነ በተዋንያንና የፊልም ባለሙያ ትልቅ እውቅናና ውገዛ ደርሶበታል። ዊል ስሚዝም ኪንግ ሪቻርድ የተባለውን ፊልም ተውኖ በምርጥ ተዋንያን አሸንፋል። ስሚዝ በአስተያየቱም አካዳሚውን፣ የፊልሙን ባልደረቦቹን፣ እና ወዳጆቹን ለክስተቱ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር እንባ ያነባው። ነገር ግን በቀጣይ ቀን ሮክን ይቅርታ ሊጠይቅ ችሏል። ጄዳ በ2018 ላይ በለቀቀችው የማህበራዊ ገፅ ቪድዮ ፀጉር የመነቃቀል በሽታ ስላለባት ሙሉ ፀጉራን እንደምትላጨው አሳስባለች።