ኮሶቮ በከፊል ተቀባይነት ያገኘ አገር ሲሆን በደቡብ አውሮፓ ይገኛል። ዋና ከተማው ፕርሽቲና ነው።

2000 ዓ.ም.ኮሶቮ ነጻነቱን ከሰርቢያ አዋጀ። ሆኖም ሰርቢያ እስካሁን ይህንን አልተቀበለም፤ በኮሶቮ ግዛት ላይ ይግባኝ ይላል።

ብዙ አገራት ኮሶቮ እንደ ነጻ አገር ቢቀበሉም፣ ሌሎች አገራት ግን በተለይም ሩስያ የሰርቢያ ግዛት ነው ብለው ለተቀባይነቱ እምቢ ብለዋል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ ኮሶቮን በይፋ ተቀባይነት ለመስጠት ተስማምቷል፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህንን ተቀባይነት በይፋ ገና አላስታወቀም።

ኮሶቮን በይፋ የሚቀበሉት አገራት (አረንጓዴ)