?እሪያ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሙሉ ጣት ሸሆኔ (Artiodactyla)
አስተኔ: የአሣማ አስተኔ Suidae
ወገን: የአሣማ ወገን Sus
ዝርያ: እሪያ S. scrofa
ክሌስም ስያሜ
Sus scrofa

እሪያ ወይም እፘ (ሮማይስጥ፦ Sus scrofa (ሱስ ስክሮፋ)፣ ግዕዝ፦ ሕንዚር) የዐሣማ ዓይነት የሆነ አውሬ ነው። ለማዳ ዐሣማ (S. scrofa domesticus) ከዚሁ ዝርያ የተገኘ ነው።

የሚገኝባቸው አገሮች በማዕከለኛ አውሮጳ፣ በሜዲቴራኔያን አካባቢ፣ በሰሜን አፍሪቃ ተራሮች፣ በእስያ እስከ ኢንዶኔዥያ ድረስ ይገኛል። እሪያ ዛሬ በኢትዮጵያ ባይገኝም በአፍሪቃ ውስጥ የሚኖር የከርከሮ (Phacochoerus africanus) ዘር ነው። በተጨማሪ ታላቅ የጫካ እሪያ (Hylochoerus meinertzhageni) የሚባለው ጸጉራም አሣማ መሳይ በጥቂት መጠን በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል።

እሪያዎች እስከ 200 ኪሎ ግራም ድረስ ክብደት ሲኖራቸው፤ እርዝመታቸውም እስከ 1.8 ሜትር ድረስ ሊሆን ይችላል። የግጭት አደጋ ቢገጥማቸው እጅግ ቁጡዎች ሲሆኑ፤ በረጅም ጥርሳቸው ጉዳት የማድረስ ችሎታ አላቸው። ነገር ግን ይህ ሁኔታ እምባዛም አይስተዋልም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንስት እሪያ ግልገሎችዋን ከጥቃት መከላከል ሲያስፈልጋት ብቻ ተግባራዊ ታደርገዋለች።

በእሪያ እና በዐሣማ መካከል ያለውን ልዩነት በተመለከተ እሪያ በጫካ ውስጥ የሚገኝ አውሬ ሲሆን፤ ዐሣማ ግን የሰው ልጅ የለመደ ነው። ዐሳማዎችም አምልጠው ወደ ጫካ ሲመለሱ ፈጥነው እሪያዎች ይሆናሉ። የእሪያ ቆዳ ባቀመቀመ ፀጉር የተሸፈነ ነው። አውራ እሪያ እንደ ከርከሮ የረዘመ ጥርስ አለው።

ጃፓን ያለ የእሪያ አደጋ ምልክት

የእሪያ መንጋ ቁጥር በተለመደ 20 እንስሶች ያህል ሲሆን ከ50 በላይ ያሉበት ስብሰባ ታይቶ ያውቃል። በተለመደ አንድ መንጋ 2 ወይም ሦስት እንስቶችና ግልገሎቻቸው ብቻ ናቸው። አውራዎቹ በብዛት ለብቻቸው እንጂ ከመፀው መርቢያ ወራት በስተቀር በመንጋው ውስጥ አይገኙም። የሚወልዱበት ወራት ጸደይ ሲሆን በተለመደ አምስት ግልገሎች ይወለዳሉ። እስከ 13 ድረስ ግን ሲቀፈቀፉ ታውቋል።

በብዛት እርያዎች የሌሊት እንስሶች ናቸው። ከማታ እስከ ንጋቱ ድረስ መኖ አሰብስበው በሌሊትም በመዓልትም ያርፋሉ። ምክንያቱም የሚያድኑዋቸው በተለይ በቀን የሚሄዱት ናቸው። እርያዎች ያገኙትን ማንኛውንም ነገር ያሕል ለምሳሌ ለውዝ፣ እንጆሪ፣ የበሰበሰ ሥጋ፣ ስሮች፣ ቆሻሻ፣ ነፍሳት፣ እንሽላሊት የመሰሉትን ትንንሽ ፍጡሮችና የአጋዘን ወይም የበግ ግልገሎች ሳይቀር ይበላሉ።

በጥንታዊት ሮማ በ3ኛው ክፍለ ዘመን የተቀረጸ የእሪያ አደንን የሚያሳይ ምስል

በአንዳንድ አገር ባሕል ስጋቸው ስለሚበላ ብቻ ሳይሆን እነርሱ ምክንያት በሰብል ወይም በእርሻ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ያድኗቸዋል።

ታሪክ ጋር በተያያዘ ልማድ የእርያ አደን በልዩ የጦር አይነት ይፈጸም ነበር። በመወጋቱ የተናደደ እሪያ በጦሩ በኩል በመግፋት አዳኙን እንዳያጠቃ ጦሩ በረጅም እጀታ ላይ የገጠመ ዛቢያ እንዲኖረው ይደረግ ነበር። የአዳኞቹ ውሾች እንኳን የቆዳ ጥሩር እንዲለብሱ ይደረግ ነበር።

ፋርስ የእርያ አዳኞች ሌላ ዘዴ ይጠቀሙ ነበር። ከሕንድ አገር ዝሆን አምጥተው እርያዎቹን አባርረው በረግረግ ውስጥ በማስገባት ይከቡዋቸው ነበር። ይህን የመሰለ ትርዒት በፋርስ በዋሻ ድንጋይ ላይ ተቀርጾ ይገኛል።

ግሪክ እና በአይርላንድ አፈ-ታሪክ ውስጥ ስለ እርያ አደን የሚያወሱ ተረቶች አሉ። በኖርስ አረማውያን እምነት አማልክቶቻቸው ለማዳ እሪያዎች ነበሯቸው። እንዲሁም በሕንድ እምነት የቪሽኑ ሦስተኛ ትንሳዔ እሪያ ነበር። በፋርስም ስለጉብዝናው ይከበር ነበር። ደግሞ እርያ ለእንግሊዝ ንጉስ ሪቻርድ 3ኛ ምልክት ነበር። እሪያም የእሪያ ራስ ምስልም በአውሮጳ የጋሻ ስእል (አርማ) ውስጥ ብዙ ጊዜ ይታያል።

በጥንት ዘመን ባንዳንድ አገሮች የእሪያ ፀጉር ለጥርስ መፋቂያ ይጠቅም ነበር። ነገር ግን የእሪያ ፀጉር ለንጽሕና የተሻለው ነገር አልነበረም።

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል