ኢሻር-ዳሙ ከ2109-2074 ዓክልበ. ግድም የኤብላ መጨረሻ ንጉሥ ነበር። የኤብላ ጽላቶች የተባሉት ሰነዶች ክምችት ይህን ዘመን ይጠቅላል።

የኢሻር-ዳሙ አባት ኢርካብ-ዳሙ ሲሆን እናቱ ንግሥት ዱሲጉ ተባለች።

በ2111 ዓክልበ. ግ. ኢብሪዩም ዋና ሚኒስትር ወይም አማካሪ ሆኖ ነበር። ንጉሡ ሕጻን እንደ ነበር ይመስላል፣ የእናቱና የኤብሪዩም ስሞች በሰነዶቹ ላይ ከስሙ ይቀድማሉና። አሦር አሁን ነጻ እንደ ነበር ይታያል፤ የአሦር መጀመርያ ንጉሥ ቱዲያ ከኤብሪዩም ጋር የስምምነት ውል ተዋዋለ። በ2100 ዓክልበ. ግድም የኤብላ ጎረቤት ናጋርማሪ ንጉሥ ተያዘ። ኤብሪዩም ከማሪ ጋር ደግሞ ስምምነት ተዋውሎ ነበር፣ የናጋር አልጋ ወራሽ ኡልቱም-ሁሁ ግን የኢሻር-ዳሙ ሴት ልጅ ልዕልት ታግሪስ-ዳሙን አግብቶ ነበር።

በ2095 ዓክልበ. ግድም ኢሻር-ዳሙ ሚስቱን ታቡር-ዳሙን አገባ። ልጆቹ ግን ከዚህ በፊት ከሌላ ቁባት ተወለዱ። በ2092 ዓክልበ. ግ. የኤብሪዩም ልጅ ኢቢ-ዚኪር በአማካሪነቱ ተከተለው። በ2089 የኢሻር-ዳሙ እናት ዱጊሱ ዓረፉ። በ2077 ዓክልበ. ግ. ኢቢ-ዚኪር የማሪ ንጉሥ ሒዳዓርን አሸነፈ። በ2074 ዓክልበ. ግ. የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ኃያላት ኤብላን አቃጠሉ።

ቀዳሚው
ኢርካብ-ዳሙ
ኤብላ ንጉሥ
2109-2074 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
የለም