ኢስላማባድ (اسلام آباد) የፓኪስታን ዋና ከተማ ነው። በካራቺ ፈንታ የመንግሥት መቀመጫ እንዲሆን በ1953 ዓ.ም. ተመሠረተ። በ1959 ዓ.ም. መቀመጫው በይፋ ወዲህ ተዛወረ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 601,600 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 33°40′ ሰሜን ኬክሮስ እና 73°08′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።