ኡር-ናንሼ ከ2314 እስከ 2284 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ መጀመርያ ንጉሥ ነበር። ቀዳሚው ሉጋል-ሻግ-ኤንጉር ንጉሥ ሳይሆን አለቃ ወይም ከንቲባ ነበር፤ ለመሲሊም ተገዥ ነበር። ከመሲሊም ዘመን በኋላ ላጋሽ ነጻ ወጣ። ኡር-ናንሼ የጉኒዱ ልጅ ነበር። ንግሥቱ መንባራ-አብዙ ተባለች። በዘመኑ ግድግዳዎች፣ ቤተ መቅደሶችና መስኖዎች እንደ ተሠሩ ይመዘገባል። ከድልሙን ጋር ንግድ ያካሄድ ነበር። በዚህ ዘመን የላጋሽ ጎረቤቶች ኡማኡር ጦርነት በላጋሽ ላይ አደረጉ፤ ኡር-ናንሼ ግን አሸነፋቸውና የኡማ ንጉሥ ፓቢልጋልቱክን ማረከው። የኡር-ናንሼ ልጅ አኩርጋል ተከተለው።

የኡር-ናንሼ ቅርስ
ቀዳሚው
ሉጋል-ሻግ-ኤንጉር
ላጋሽ ገዥ
2314-2284 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አኩርጋል