አኑራደፑረ መሃቪሃረአኑራደፑረስሪ ላንካ የሚገኝ ጥንታዊ የቡዲስም ትልቅ ገዳምቤተ መቅደስ ነው። በ244 ዓክልበ. በንጉስ ደቫናምፒያ ቲሣ ተመሠረተ።

ቤተ መቅደሱ

የ«መሃ ቪሃረ» ትርጉም ከፓሊኛ «ታላቅ ገዳም» ሲሆን ከቡዲስት ገዳም በላይ ለቡዲስም ኅብረተሠብ ተከታዮች እንደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት አገልግሏል። ከ244 ዓክልበ. እስካሁን ወይም 2,254 ዓመታት ያህል፣ ይህ አኑራደፑረ መሃቪሃረ ለጤራቫዳ ቡዲስም ዓለም የጤራቫዳ እምነትና ርዕዮተ አለም ጠባቂዎች ሆነዋል። ስለዚህ ዛሬ ከሚገኙት ከዓለም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እርሱ ከሁሉ ጥንታዊው የሆነው ሊባል ይችላል።

ከ80 ዓክልበ. እስከ 1157 ዓም. ድረስ፣ ሌላ ተወዳዳሪ መሃ-ቪሃረ «አበየጊሪ ቪሃረ» በዚያው ከተማ ይገኝ ነበር። እርሱ ያስተማረው ጤራቫዳ እምነት ግን ከሌላው ቡዲስም ወገን ከመሃያነ ቡዲስም ወገን ትምህርቶች ጋር የተቀላቀለ ነበር፤ ስለዚህ በ1157 ዓም ሃራ ጤቆች ተብለው ያው ቪሃረ በንጉሥ ፩ ፐራክረመባሁ ትዕዛዝ ተዘጋ።

እንዲሁም በ270 ዓም ግድም የነበረው ንጉሥ መሃሴነ የመሃያነን ወገን ስለ ደገፈ፣ መሃቪሃረውን አጥፍቶ አዲስ ሦስተኛ ተቋም ጄተቨና በአኑራደፑረ ከተማ መሠረተ። ከዚህ ትንሽ በኋላ ያው ንጉሥ ዳግመኛ መሃቪሃረውን አሠራ። ሦስተኛው ተቋም ጄተቨና ደግሞ ከ270 እስከ 1157 ዓም ድረስ ቆመ።

ቻይና ተጓዥ ፋሥየን ተቋሙን በ398 ዓም በጎበኘው ጊዜ 3,000 ተማሮች መኖኩሶች (ቢኩዎች) እንደ ተገኙ ጻፈ። በዚያውም ወቅት፣ ከአለም ዋና ዩኒቨርስቲዎች አንድ ነበረ። ሆኖም ፋሥየን በዚያው አመት ተወዳዳሪው አበየጊረ 5,000 ቢኩዎች እንደ ነበሩት መሠከረ፣ ከ1157 ዓም በፊት ነገሥታቱ ለአበየጊረ አድልዎን ያሳዩ ነበርና። ከ1157 ዓም ጀምሮ ግን ጤራቫዳ ብቻ ተደገፈና ሌሎቹ ሁለት ተቋማት ወደ መሃቪሃረ ተጨመሩ።

ተቋሙ የሚያስተምረው በተለይ ለጤራቫዳ እምነት ተከታዮች የሚገቡት ጽሁፎችና ኑሮ ዘዴዎች በተመለከተ ነው።