አርጌንቶማጉስሮሜ መንግሥት ዘመንና ከዚያም በፊት የጋሊያ (አሁን ፈረንሳይ አገር) ከተማ ነበር። ቢቱሪጌስ የተባለ ጎሣ በዙሪያው ይኖር ነበር። 42 ዓ.ም. አካባቢ ሮማውያን ያዙት። ፍርስራሹ ከዛሬው አርዠንቶን-ሱር-ክሮይዝ አጠገብ ይገኛል።

አርጌንቶማጉስ
የሮማውያን ቴያትር ፍርስራሽ
ሥፍራ
አርጌንቶማጉስ is located in France
{{{alt}}}
መንግሥት የሮሜ መንግሥት
ዘመን 50-400 ዓ.ም. ገደማ
ዘመናዊ አገር ፈረንሳይ
ጥንታዊ አገር ጋሊያ

አርጌንቱም ማለት «ብር» ሲሆን የማጉስ ትርጉም «ገበያ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚያ ዘመን አያሌ ገበዮችና መንደሮቹ «-ማጉስ» በሚለው ስም ይጨረሱ ነበር። በአንድ ትውፊት ግን ማጉስ ከተሞቹን የመሠረተው የጥንት ንጉሥ ስም ነበረ።